1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምርጫ በአምቦ እና አካባቢው

ሰኞ፣ ሰኔ 14 2013

ዛሬ በምዕራብ ሸዋ ዋና ከተማዋ በአምቦ ሲካሄድ በዋለው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ምንም እንኳ ብቸኛ ተፎካካሪ ሆኖ የቀረበው ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ቢሆንም ምርጫውን ቁጥራቸው የማይናቅ ነዋሪዎች ከማለዳው ጀምሮ ወጥተው የመራጭነት ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

https://p.dw.com/p/3vIfC
Parlamentswahl in Äthiopien 2021
ምስል S. Getu/DW

«ለምርጫ የቀረበው ብልጽግና ነው»

ዛሬ በምዕራብ ሸዋ ዋና ከተማዋ በአምቦ ሲካሄድ በዋለው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ምንም እንኳ ብቸኛ ተፎካካሪ ሆኖ የቀረበው ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ቢሆንም ምርጫውን ቁጥራቸው የማይናቅ ነዋሪዎች ከማለዳው ጀምሮ ወጥተው የመራጭነት ድምጻቸውን ሰጥተዋል። አምቦን ጨምሮ በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች ላይ ቅኝት ያደረገው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ ከምርጫው ዋዜማ ጀምሮ ከፍተኛ የፀጥታ ኃይሎች እንቅስቃሴን በአከባቢው ማስተዋሉን ገልጿል፡፡ ዛሬ መራጮች በየምርጫ ጣቢያው ወጥተው ሲመርጡም ከተማዋ በእጅጉኑ ፀጥታ ተጭኗት እንቅስቃሴ አልባ ሆና ነው ያረፈደችው፡፡ በአምቦም ሆነ በዙሪያዋ ባሉ እንደ ጉደርና ጊንጪ እንዲሁም ሌሎች ከተሞች ላይ ምንም አይነት የትራንስፖርት እንቅስቃሴም አልተስተዋለም፡፡ ከሰዓቱን ግን በመንገድ ላይ የሚታዩ ሰዎች ቁጥር የተሻለ ሆኖ ተስተውሏል፡፡

በምዕራብ ሸዋ ዞን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 18 እጩዎች ለክልል ምክር ቤት ደግሞ 43 እጩዎች ናቸው የተመዘገቡት፡፡ በዚህ ዞን በቡራዩ አንድ የህ/ተ/ም/ቤት እጩ ካስመዘገበው አንድነትና እኩልነት እንዲሁም ለህ/ተ/ም/ቤት አንድ እጩ እና ለክልል ምክር ቡት አንድ እጩ ካስመዘገበው የኦሮሞ እኩልነትና ነጻነት ፓርቲ ውጩ በሁሉም የምርጫ ክልሎች ብልጽግና ፓርቲ ብቸኛ ተወዳዳሪ መሆኑን ከዞኑ ምርጫ አስተባባሪ ተረድተናል፡፡

ስዩም ጌቱ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ