1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምርጫ በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል

ሰኞ፣ ሰኔ 14 2013

በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል   ሀገራዊ ምርጫ ከማለዳ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ  ሲካሄድ ቆይተዋል፡፡  በአሶሳ ከተማ ዘጋቢያችን ከጠዋት እስከ 6 ሰዓት በተዘዋወረበት የምርጫ ጣቢያዎች ዜጎች ሰላማዊ በሆነ መልኩ ምርጫ ማካዳቸውን ነግረውታል። 

https://p.dw.com/p/3vI1d
Äthiopien Asosa | Parlamentswahl 2021
ምስል N. Dessalegn/DW

ከ366ሺ በላይ ዜጎች ለመምረጥ ተመዝግበዋል

በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል   ሀገራዊ ምርጫ ከማለዳ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ  ሲካሄድ ቆይተዋል፡፡  በአሶሳ ከተማ ዘጋቢያችን ከጠዋት እስከ 6 ሰዓት በተዘዋወረበት የምርጫ ጣቢያዎች ዜጎች ሰላማዊ በሆነ መልኩ ምርጫ ማካዳቸውን ነግረውታል።  ዘጋቢያችን ወጣቶች፣ ሴቶች እንዲሁም  የሀገር ሽማግለዎች  በድምጽ አሰጣጥ ሂዴቱ ላይ ሲሳተፍ ከሁሉም ስፋራ ተመልክቷል፡፡ ያነጋገርኳቸው የመንግስት እና የተቋሚ ፓርቲ ታዛቢዎችም ምርጫው ህጋዊ ሂዴቱን በጠበቀ መልኩ እየተከናወነ እንደሚገኝ  ተናግረዋል፡፡  ካየዋቸው ስድስት ምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ አብዛኞቹ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ማስክ ያደረጉ ሲሆን አንድአንዶች ደግሞ ትኩረታቸውን ምርጫ ላይ ብቻ ያደረጉ ይመስላል ምንም ማስክ  ያላደረጉ መራጮችም  አሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከሰዓት በኃላበአሶሳ ዞን 102 በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እጥረት ስላጋጠማቸው እንዲላክላቸው እየተጠባበቁ እንደሚገኙ በምርጫ ቦርድ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ታደሰ ለማ በስልክ ተናግረዋል፡፡ በምርጫ ቦርድ መረጃ መሰረት በአሶሳ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚወዳደሩ ሲሆን የብልጽግና ፓርቲ፣ የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ፣የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ኢዜማ፣ እናት ፓርቲ እና መኢአድ ይገኙበታል፡፡

በአሶሳ እና አሶሳ ዞን 302 የምርጫ ታጣቢያ የሚገኙ ሲሆን ከ366ሺ በላይ ዜጎች ደግሞ በዛሬው  ዕለት ድምጽ  ለመስጠት ካርድ ስለመውሰዳቸው  በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡ ካሉት  ምርጫ ጣቢያዎች መካከል  61 የሚደርሱት በአሶሳ ከተማ እና ዙሪያ ይገኛሉ፡፡ ዛሬ ማለዳ 12፤00 ጀምሮ በተዘዋርኩባቸው ስድስት የምርጫ ጣቢያዎች   ካርድ የወሰዱ ነዋሪዎች ድምጽ ለመስጠት የተሰበሰቡበት  ረጃጅም ሰልፎች ይታያሉ፡፡  አቶ አሰፋ ካሳሁን    የአሶሳ ከተማ ነዋሪና በምርጫ የተሳተፉ ሲሆን የምርጫ ሂዴቱ ሰላማዊ እና ግልጽ እንደነበር አመልክቷል፡፡ 

Äthiopien Asosa | Parlamentswahl 2021
ምስል N. Dessalegn/DW

ወ/ሮ አልማዝ መንግስቱ እና ወ/ሮ ጥሩወርቅ ካሳሁን የአሶሳ ከተማ 02 ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ በምርጫ ላይ መሳተፋቸውን ገልጸዋል፡፡  በዛሬው ዕለት በተካሄደው ምርጫ ያለምንም ጫና ድምጽ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡  የሚመረጠው መንግስትም ለአካል ጉዳተችና አቅመ ደካሞች ትኩረት እንዲሰጥ እና መሰረታዊ ችግሮቻቸውን እንንዲፈታላቸውም ያላቸውን ሀሳብ ጠቁመዋል፡፡  በምርጫ አስፋጻሚዎች በኩል  ገለጻዎች ሲደረጉ እና ለአቅመ ደካሞች እና አካል ጉዳተኞች በድምጽ አሰጣጣቱ ሂዴቱ ላይ  ቅዲሚያ  ሲስጣቸውም  በአሶሳ ከተማ በቀበሌ 2  በሚገኘው ምርጫ ጣቢያ ተመልክቻለሁ፡፡

ያነጋገርኳቸው በአሶሳ  ከሚወዳሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የቤኒሻንል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ እና ብልጽግ ፓርቲ ተወካይ እና ታዛቢዎች የምርጫ ሂዴቱ ህጉን ጠብቆና ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን   አስታውቋል፡፡

በ2007 ዓ.ም በተደረገው 5ኛ ሀገራዊ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ደረጃ 340ሺ188 ዜጎች በምርጫ የተሳተፉ ሲሆን በዘንደሮ 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ ላይ ደግሞ  ከ366ሺ በላይ ዜጎች በምርጫ ለመሳተፍ ካርድ መውሰዳቸውን ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅ/ጽ/ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡ በክልሉ በጸጥታ ችግር በዛሬው ዕለት ምርጫ ያልተካሄዳባቸው መተከል ዞንና ካማሺ ዞን ጳጉሜ 1/2013 ዓ.ም ምርጫ  እንደሚካሄድም  ተገልጸዋል፡፡

ነጋሣ ደሳለኝ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ

ኂሩት መለሰ