1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምርጫ በባሕር ዳርና አማራ ክልል

ሰኞ፣ ሰኔ 14 2013

በባሕር ዳር ከተማ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች መራጩ በከፍተኛ ሁኔታ ወጥቶ ሲመርጥ ዉሏል። በከተማዋ ማር ዘነብ ቀበሌ 2ሐ ምርጫ ጣቢያ በጠዋት ከመረጡ ነዋሪዎች መካከል ሁለቱ በሰጡት አስተያየት ሂደቱ መልካም ነው።

https://p.dw.com/p/3vIGt
Äthiopien | Parlamentswahl
ምስል A. Mekonnen/DW

 

በባሕር ዳር ከተማ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች መራጩ በከፍተኛ ሁኔታ ወጥቶ ሲመርጥ ዉሏል። በከተማዋ ማር ዘነብ ቀበሌ 2ሐ ምርጫ ጣቢያ በጠዋት ከመረጡ ነዋሪዎች መካከል ሁለቱ በሰጡት አስተያየት ሂደቱ መልካም ነው። በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ካሉ ሦስት የምርጫ ክልሎች መካከል ዛሬ በዳህናና ዝቋላ የምርጫ ክልሎች ምርጫ እየተካሄደ ነው፣ የብሔረሰብ አስተዳደሩ ምርጫ ቦርድ ኃላፊ አቶ ሹመት ጥላሁን እንዳሉት ምርጫው ያለምንም እንከን እየተካሄደ ነው። ከዚህ በተጨማሪም በምዕረብ ጎንደር ዞን መተማ ከተማ፣ በደቡብ ወሎ ደሴ ከተማ፣ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የእንጅባራ ከተማና በምስራቅ ጎጃም ዞን የሞጣ ከተማ ነዋሪዎችን አስተያየትንም ጠይቀን መልካም እንደሆነ ነግረውናል። በአማራ ክልል 7 ሚሊዮን 400 ሺህ መራጮች ካርድ ወስደዋል፣ 138 የምርጫ ክልሎች ሲገኙ 12 ሺህ 199 የምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ ተዘጋጅተዋል፣ 18 የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ለክልልና ለተወካዮች ምክር ቤት ወንበሮች ይወዳደራሉ።


ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ