1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማንነት ላይ አነጣጥሮ የቀጠለው ጥቃት

እሑድ፣ ታኅሣሥ 18 2013

ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መድረሳቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ከቅርብ ወራት ወዲህ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጥቃቱ ተባብሶ መቀጠሉ ታይቷል።

https://p.dw.com/p/3nDpz
Karte Äthiopien Metekel EN

የታኅሣስ 18 ቀን 2013 እንወያይ ፦ማንነት ላይ አነጣጥሮ የቀጠለው ጥቃት

ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መድረሳቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ከቅርብ ወራት ወዲህ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጥቃቱ ተባብሶ መቀጠሉ ታይቷል። ከዚህ ቀደም ሶማሌ ክልል፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብና አማራ ክልልም ጥቃቶች መድረሳቸው ቢዘገብም ጥፋተኞቹ ለፍርድ ቀርበው ለጉዳተኞች ተክሰው ጉዳዩ በዝርዝር ተጣርቶ የተገኘው ውጤት አለመሰማቱ ድርጊቱ በሌሎች አካባቢዎች ለመቀጠሉ ምክንያት ሆኗል የሚሉ አሉ። በሌላ በኩል ድርጊቱ በተለይም ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ተባብሶ መቀጠሉ የሚታይ ቢሆንም የበርካታ መገናኛ ብዙሃንንም ሆነ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማትን ትኩረት ያን ያህል ሲስብ አልታየም። የገዢው ፓርቲ ብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት ስብሰባ አካሂዶ ባወጣው መግለጫ በተለያዩ አካባቢዎች ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለማስቆም ርምጃ እንደሚወስድ አመልክቷል። ዶቼ ቬለ በዚህ ሳምንት ማንነት ላይ አነጣጥሮ የቀጠለው ጥቃት፣ የመንግሥት ወይም ገዢው ፓርቲ አቋምና መፍትሄው ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል። ሙሉ ውይይቱን ከድምጽ ማዕቀፉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ