1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማነጋገር የጀመረው የአዲሱ የብር ኖቶች ገፅታ

ረቡዕ፣ መስከረም 13 2013

በአዲሶቹ የብር ኖቶች ላይ የሚታየው ልዩነት ተራ የሕትመት ችግር እንጂ ተመሳስሎ የተሠራ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።  የባንኩ የከረንሲ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አበበ ሰንበቴ ለዶቼ ቬለ በኅብረተሰቡ ውስጥ እየተነዙ ያሉት ውዥንብሮች ትክክል አይደሉም ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3iuEM
Äthiopien Addis Abeba | Neue Währung | Birr
ምስል Yohannes Gebregziabher/DW

«የሚነዛው ውዥንብር ትክክል አይደለም»

በአዲሶቹ የብር ኖቶች ላይ የሚታየው ልዩነት ተራ የሕትመት ችግር እንጂ ተመሳስሎ የተሠራ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። በብሮቹ ላይ ታዩ የሚባሉት አለመመሳሰሎች የሀገርን ኤኮኖሚ ለማናጋት የተበተነ የሀሰት ገንዘብ ነው የሚል ያልተረጋገጠ ወሬን ወደማናፈስ አስገብቷል።  የባንኩ የከረንሲ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አበበ ሰንበቴ ለዶቼ ቬለ በኅብረተሰቡ ውስጥ እየተነዙ ያሉት ውዥንብሮች ትክክል አይደሉም ብለዋል። ገንዘቡ ከተለወጠ በዚህ በአጭር ጊዜ አጭበርብሮ አስመስሎ ለመሥራትም ጊዜ እንደሚያሻም ተናግረዋል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ