1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሙሴ ቬኒ የጠሩት ጉባኤ እና የብሊንከን የአፍሪቃ ጉብኝት 

ማክሰኞ፣ ኅዳር 7 2014

የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በየነ መንግስታት አባል ሐገራት መሪዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉ ጦርነት በሰላም ስለሚያበቃበት ጉዳይ ለመነጋገር ለዛሬ ይዘዉት የነበረዉ ቀጠሮ  ተሰረዘ። የኢጋድ አባል ሐገራት መሪዎች ዛሬ ካምፓላ-ዩጋንዳ ዉስጥ ተገናኝተዉ እንዲነጋገሩ የጠሩት የዩጋንዳዉ ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴ ቬኒ ነበሩ።

https://p.dw.com/p/434JC
Großbritannien London 2020 | Yoweri Museveni, Präsident Uganda
ምስል Henry Nicholls/REUTERS

የአሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪቃ ጉብኝት ዓላማዉ ምንድን ነዉ?

የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በየነ መንግስታት (IGAD) አባል ሐገራት መሪዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉ ጦርነት በሰላም ስለሚያበቃበት ብልሐት ለመነጋገር ለዛሬ ይዘዉት የነበረዉ ቀጠሮ  መሰረዙ ተሰምቶአል። የኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ስለገጠሙት ጦርነት የኢጋድ አባል ሐገራት መሪዎች ዛሬ ካምፓላ-ዩጋንዳ ዉስጥ ተገናኝተዉ እንዲነጋገሩ የጠሩት የዩጋንዳዉ ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴ ቬኒ ነበሩ። ጉባኤዉ የተላለፈበትን ምክንያትም ሆነ የሚደረግበት ቀን አልጠቀሰም። በኬንያ ነዋሪ የሆነዉ ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ ቻላቸዉ ታደሰን የብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝት አጠቃላይ ዓላማ፤ ኬንያ የትግራዩን ግጭት ለመፍታት ሚና እንድትጫወት ብሊንከን ተስፋ ስለማድረጋቸው እና አሜሪካ እና ኬንያ በአሁኑ ሰዓት ቅድሚያ ስለሚሰጧቸው የጋራ ጉዳዮችን በተመለከተ ጠይቀነዋል። 

ቻላቸዉ ታደሰ 
ኂሩት መለሰ