መኪና አልባ ቀናት በአዲስ አበባ
በኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ በወር 6 ቀናት ከተማዋን ከተሽከርካሪ ነፃ ማድረግ ፤የዓየር ንብረት ብክለት ለመከላከልና ተሽከርካሪ ያልሆኑ ሌሎች የመጓጓዣ አገልግሎቶችን ለማበረታታት በመንግስት የተቀረፀ መርሃ ግብር ነዉ።
ፋታ መውሰጃ ጊዜ
ከ4 ሚሊዮን ህዝብ በላይ መኖሪያ የሆነችዉ አዲስ አበባ በጎርጎሮሳዊዉ እሁድ ግንቦት 12 ቀን አብዛኛዉ የከተማዋ ክፍል ለተሽከካሪዎች ክፍት ቢሆኑም ፤ ተዘግተዉ ነበር የሰነበቱት።ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ለሚታይባት አዲስ አበባ በዚህ ቀን አነስተኛ የትራፊክ እንቅስቃሴ ይታይ ነበር።ይህ መርሃ-ግብር ብክለትን ለመቆጣጠር በቂ ባይሆንም ብዙዎች ቀኑን በደስታ ለማሳለፍ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ያዩታል።
የኳስ ጊዜ
ከተሽከርካሪ ነፃ ቀን አካላዊ እንቅስቃሴን ለማድረግ የሚያበረታታ ሆኗል።እግር ኳስ በኢትዮጵያ ተወዳጅ ስፓርት ነዉ።የእንግሊዝ የእግር ኳስ ክለቦች በሀገሪቱ ተወዳጅ ናቸዉ።በመሆኑም እሁድ እሁድ ብዙ ሰዉ ጨዋታዎቹን ይመለከታቸዋል።የሀገር ዉስጥ ጨዋታዎችም ተመልካች አላቸዉ።
የአካላዊ እንቅስቃሴ ቀን
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በማለዳ ተነስተዉ በሙዚቃ የስፖርት ልምምድ ማድረግ የተለመደ ነዉ።በሀገሪቱ ባህል ሯጮችን ከንጋቱ 10 ስዓት መመልከትም የተለመደ ነዉ።
ዓይን የሚቆጠቁጥ ጭስ
መስቀል አደባባይ አብዛኛዉን ጊዜ የትራፊክ መጨናነቅ ከሚታይባቸዉ የከተማዋ ክፍል አንዱ ነዉ። ከፍተኛ የሙዚቃ ድምፅና ጭስ በከተማዋ የተለመደ ገፅታ ነዉ።አዲስ አበባ በብክለት ከናይጄሪያዋ ሌጎስ ቀጥሎ በአፍሪቃ 4ኛዋ ከተማ ነች።አረንጓዴ መናፈሻዎችም ብዙ የላትም።ለብስክሌተኞች የሚሆን መንገድም የለም።ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የወንዞችን ዳርቻ ለማልማትና የመዝናኛ ቦታዎች እንዲሁም የብስክሌት መንገዶችን ለማዘጋጀት ከፍተኛ ፍላጎት እላቸዉ።
«መኪና ለሰዉነት ብስክሌት ለመንፈስ »
የከተማዋ አስተዳደር በቅርቡ ለሠራተኞቹ 600 ብስክሌቶችን ለግሷል። አብርሃም ብስክሌተኞችን ለማበረታት ለመጓጓዣ አገልግሎት ጽሕፈት ቤቱ የበጎ ፈቃደኛ አገልግሎት ይሰጣል። ነገር ግን «አዝማሚያዉ መኪና ወደማዘውተር እየሄደ ነዉ» ይላል። እንዲያም ሆኖ «የመኪና አልባ 6 ቀናት » መርሃ ግብርን የሚደግፉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነዉ። መርሃ-ግብሩ ሥራ ላይ ከዋለም ተጨባጭ ልዩነት ሊፈጥር እንደሚችል የሚያሳይ ነዉ። የሚል እምነት አለዉ።
የ«ስኬተሮች» ገነት
በአዲስ አበባ ከተማ የስኬቲንግ ስፖርት ማህበረሰብ እያደገ መጥቷል። ይህንን በከተማ የሚዘወተር ስፖርት መንግስታዊ ያልሆነዉ ድርጅት «ስኬት ኢትዮጵያ» ዝቅተኛ ገቢ ላላቸዉ ልጆችና ለአካል ጉዳተኞች «ስኬት ቦርድና» መደበኛ ስልጠና ይሰጣል።«በመኪና ነጻ ቀን ከልጆች ጋር እንወጣለን። «ስኬት ቦርድ» በመስጠት እንዴት መንሸራተት እንደሚችሉም እናስተምራለን። ይላል ፤ሚኪ ከኢትዮጵያ ስኬት ።የሆነዉ ደግሞ ስፖርቱን የመልመድ ባህል እየጨመረ በመምጣቱ መሆኑን ይገልፃል።
የጎዳና ዳንስ
ለ«ደሲቲኖ ዳንስ» ህዝብ በሚሰበሰብባቸዉ ቦታዎች ዳንስ መለማመድ የተለመደ ሆኗል። ድርጅቱ ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ዉስጥ የአካል ጉዳተኞችና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ ልጆች ዉዝዋዜ ያስተምራል።መስራቾቹ ጁናድና አዲሱ የዉዝዋዜ ባለሙያዎች ናቸዉ።ዳንስ የጀመሩት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ነዉ ።በአሁኑ ጊዜ የባህላዊና ዘመናዊ ዳንሶችን በመቀለቀል ሌላ ዳንስ ፈጥረዋል።
የመጓጓዣ አገልግሎት ችግር
አዲስ አበባ የኤለክትሪክ ባቡር ያላት ብቸኛዋ የአፍሪቃ መዲና ነች፤ምንም እንኳ በብቃት ችግር ተደጋጋሚ ወቀሳ ቢቀርብበትም። የባቡር መስመሩ ከቻይና በተገኘ የ445 ሚሊዮን ወይም የግማሽ ቢሊዮን ዶላር ነዉ የተገነባዉ።የባቡር መስመሩ ለአየር ንብረት ብክለት ተጨባጭና ትልቅ ተፅዕኖ ባይኖረዉም፤ከመኪና ባሻገር ሌላ አማራጭ የመጓጓዣ አገልግሎት ሊሆን ይችላል።
ከፍተኛ ስጋት
ብዙዎች ኢትዮጵያዉያን መኪና ለመግዛት አቅም የላቸዉም።ምክንያቱም መኪና ለማስገባትና ለባለቤትነት የሚከፈለዉ ቀረጥ ከፍተኛ ነዉ።ዜጎች በዋጋዉ መናር መንግስትን ያማርራሉ።ኢትዮጵያ እስካሁን በዓለም ላይ አነስተኛ ቁጥር ያለው ተሽከርካሪ ካላቸዉ ሀገሮች ዉስጥ አንዷ ነች።በአዲስ አበባ ከተማ የሚኒባስ ታክሲዎች ከፍተኛ የመጓጓዣ አገልግሎት ሰጪዎች ናቸዉ።ከነዚህ ዉስጥ አብዙዎቹ በየቀኑ አቧራማ በሆኑ መንገዶች ያጓዛሉ።