1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መንግስትና ነጋዴዎች ስለ ዋጋ ንረት ተወያዩ

ሰኞ፣ ነሐሴ 27 2011

ምክንያት የለሽ የሸቀጦች የዋጋ ንረት የፈጠረው የኑሮ ውድነት የሸማቹን ህብረተሰብ አኗኗር መፈታተኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ።  ሚኒስቴሩ ዛሬ ከአምራቾች ፣ አስመጭዎችና ነጋዴዎች ጋር ባደረገው ውይይት የዚህ ምክንያት የለሽ የዋጋ ንረት ሊገታ በሚችልበትና ፍትሃዊ ግብይት በሚዘረጋበት ጉዳይ ዙሪያ ተወያይቷል።

https://p.dw.com/p/3OtX4
Lebensmittel im Bahir Dar lokalen Markt  Äthiopien
ምስል DW/A. Mekonnen

መንግስትና ነጋዴዎች ስለ ዋጋ ግሽበት ተወያዩ

ምክንያት የለሽ የሸቀጦች የዋጋ ንረት የፈጠረው የኑሮ ውድነት የሸማቹን ህብረተሰብ አኗኗር መፈታተኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ።  ሚኒስቴሩ ዛሬ ከአምራቾች ፣ አስመጭዎችና ነጋዴዎች ጋር ባደረገው ውይይት የዚህ ምክንያት የለሽ የዋጋ ንረት ሊገታ በሚችልበትና ፍትሃዊ ግብይት በሚዘረጋበት ጉዳይ ዙሪያ ተወያይቷል።
ከውይይቱ በኋላ ይህ ህገ ወጥ ተጠቃሚነት ካልተገታም ህጋዊ እርምጃ በሚወሰድበት አካሄድ ላይም ምክክር አድርጓል።

የዋጋ ንረቱ በመሰረታዊ የምግብ የግብርና ምርቶች ፣ የኢንዲስትሪ ውጤቶችና በግንባታ ፍእቃዎች ላይ በከፍተኛ መጠን ማሻቀቡን ሚኒስቴሩም ፣ ነዋሪዎችም ለ ዶቼ ቬለ አረጋግጠዋል። የህገ ወጥ ደላላዎች ረጅም እጅም ገበያው በተጋነነ ግብይት እንዲታመስ ዋነኛ ምክንያት ናቸው ተብሏል።
ሰለሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ