1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መቀሌ አካባቢ በቦምብ ተመታ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 26 2013

የኢትዮጵያ የጦር ጄቶች ዛሬ አመሻሽ ላይ የትግራይ ርዕሠ ከተማ መቀሌ አካባቢን በቦምብ መደብደባቸዉን የትግራይ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ።የክልሉ የመንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ በክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ባሰራጨዉ መግለጫ  ጄቶቹ መቀሌ አካባቢ ቦምብ ጣሉ ከማለት ባለፍ ትክክለኛዉን ሥፍራ አልጠቀሰም።

https://p.dw.com/p/3kvTc
Karte Sodo Ethiopia ENG

ጄቶቹ መቀሌ አካባቢ ቦምብ ጣሉ ከማለት ባለፍ ትክክለኛዉን ሥፍራ አልጠቀሰም

የኢትዮጵያ የጦር ጄቶች ዛሬ አመሻሽ ላይ የትግራይ ርዕሠ ከተማ መቀሌ አካባቢን በቦምብ መደብደባቸዉን የትግራይ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ።የክልሉ የመንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ በክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ባሰራጨዉ መግለጫ  ጄቶቹ መቀሌ አካባቢ ቦምብ ጣሉ ከማለት ባለፍ ትክክለኛዉን ሥፍራ አልጠቀሰም።የአዲስ አበባና የመቀሌ ወኪሎቻችን እንደጠቀሱት መግለጫዉ፣ በጥቃቱ የደረሰ ጉዳት ሥለመኖር አለመኖሩ ያለዉ ነገር የለም።ይሁንና ጥቃቱን «የትግራይ ሕዝብን ለማንበርከክ» ያለመ ብሎታል።

ዮኃንስ ገብረግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ