መረጋጋት የታየባት ጎንደር
ሰኞ፣ ጥቅምት 10 2012የከተማው የሰላምና የሕዝብ ደህንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋ መኮንን ዛሬ ጎንደር ከተማ ውስጥ ለዶይቼ ቬለ አንደገለፁት ሰሞኑን በጎንደርና አካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ምክንያት ተጠርጥረው በሕግ ጥላ ስር ከቆዩት 119 ተጠርታሪዎች መካከል ጉዳቸው ተጣርቶ 58ቱ ተለቅቀዋል። ኃፊው እንዳሉት መንግሥት በአካባቢው ሰላም ለማረጋገጥ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ በከተማው የንግድ እንቅስቃሴና አጠቃላይ ሰላሙ እየተመለሰ ነዋሪውም መደበኛ ሥራውን በመስራት ላይ አንደሆነ አመልክተዋል። ኅብረተሰቡ መንግሥት ያወጣውን መግለጫ እንደተቀበለው አመልክተው መዘግት አልነበረበትም የሚል ቅሬታ ግን አንደነበረው አስረድተዋል።
ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች መካከል መምህር ዘላለም አዲስም መግለጫው መዘግት እንዳልነበረበት አመልክተው ቢሆንም አሁን ለተገኘው ሰላም አስተዋጽኦ አለው ነው ያሉት። በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት መድረሱንና ሰዎች መፈናቀላቸውን የተተናገሩት አቶ ተስፋ የሟቾችንም ሆነ የተፈናቃዮችን ቁጥር አልገለፁም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በከተማው አንጻራዊ ሰላም መኖሩንና ወጣቶችም ሰላሙን ለማስቀተል እየሠሩ መሁኑን የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች አመልክተዋል። አስተያታቸውን ከሰጡኝ ነዋሪዎች መካከል አንዱ አቶ እንዳለው ፈቃዴ አንዱ ናቸው። ወጣቱ ቀን እና ሌሊት እየሠራ ነው። አልፎ አልፎ የተኩስ ድምጽ ቢሰማም አሁን የተሻለ ነገር አንዳለ የገለፁት ደግሞ አቶ መሳፍንት ወርቁ ናቸው። ሌላው ነዋሪ አቶ ጌቱ ወርቁ አንደሚሉት የተገኘውን ሰላም ለማስቀጠል ወጣቱ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር መሥራት ይገባዋል። ወደ ጎንደር የተጓዘው የባሕር ዳሩ ዘጋቢያችን በላከው ዘገባ ጠቅሷል።
ዓለምነው መኮንን
ሸዋዬ ለገሠ
ተስፋለም ወልደየስ