1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መልካም ልደት አንጌላ ሜርክል!

ረቡዕ፣ ሐምሌ 10 2011

የጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ዛሬ 65 ኛ የልደት በዓላቸዉን ያከብራሉ። በጎርጎረሳዊዉ ሐምሌ 1፤ 1954 ዓመት የተወለዱት መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የመራሒ መንግሥትነቱን ስልጣን የያዙት በጎርጎረሳዊዉ 2005 ዓ,ም ነዉ።

https://p.dw.com/p/3MBQ8
Angela Merkel empfängt Mette Frederiksen
ምስል Reuters/H. Hanschke

 

የጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ዛሬ 65 ኛ የልደት በዓላቸዉን ያከብራሉ። በጎርጎረሳዊዉ ሐምሌ 1፤ 1954 ዓመት የተወለዱት መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የመራሒ መንግሥትነቱን ስልጣን የያዙት በጎርጎረሳዊዉ 2005 ዓ,ም ነዉ። በርጋታና በጥልቅ አስተዋይነት ጀርመንን እንደሚያስተዳድሩ የሚነገርላቸዉ አንጌላ ሜርክል ፤ በስልጣን ጊዜያቸዉ አዉሮጳን አጥለቅልቆት የነበረዉን የስደተኞች ጎርፍ ሃገራቸዉ ጀርመን በቀዳሚነት ተሳታፊ እንድትሆን እና የአንበሳዉን ድርሻ እንድትይዝ በመፍቀዳቸዉ በተለይ በዉጭዉ ዓለም ከፍተኛ ዝናን አትርፈዋል። ሜርክል አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ከሐገራት መሪዎች እና እንግዶች ጋር እንደቆሙ ሰውነታቸዉ በተከታታይ መርገፍገፉ የጤናቸዉን ሁኔታ አጠራጣሪ አድርጎት ሰንብቶ ነበር ። ሜርክል ግን አሉ ጤንነቴን እጠብቃለሁ እጠነቀቃለሁም! መልካም ልደት መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል! በጀርመንኛዉም የመልካም ልደት መግለጫችን ይድረሳቸዉ!

Liebe Frau Merkel, herzlichen Glückwunsch zum Geburtstag!!!