1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሕወሓት ከሰሞኑ ከፍተኛ ጥቃት ሰንዝሯል፤ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 20 2014

ሕወሓት ባሰማረው ከፍተኛ "የመንጋ" ያሉት ወራሪ ኃይል ከሰሞኑ ከፍተኛ ጥቃት መሠንዘሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት ሚንስትሩ ለገሰ ቱሉ ተናገሩ። ከመደበኛ የጦርነት ባሕሪ የወጣውን ጥቃት ለመመከት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ መቅረቡንም ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/42NZR
Äthiopien Addis Abeba | Legesse Tulu
ምስል Solomon Muchie/DW

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጉዳዮች አገልግሎት ሚንስትር የሰጡት መግለጫ

ሕወሓት ባሰማረው ከፍተኛ "የመንጋ" ያሉት ወራሪ ኃይል ከሰሞኑ ከፍተኛ ጥቃት መሠንዘሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት ሚንስትሩ ለገሰ ቱሉ ተናገሩ። ከመደበኛ የጦርነት ባሕሪ የወጣውን  ጥቃት ለመመከት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ መቅረቡንም ገልጸዋል። "የወገን ጦር ውስጥ ተቆርቋሪ በመምሰል ባንዳ ሆነው የሚያገለግሉ ኃይሎች አሉ" ያሉት ሚንስትሩ የመከላከያ ኃይል እና የፀጥታ ኃይሎች ሥራዎቻቸውን ለመሥራት ሲንቀሳቀሱ ባንዳ ባሏቸው አካላት የማወክ ፣የማገድ፣ እንቅፋት የመሆን ሁኔታ መኖራቸውን ገልፀዋል። ሚንስትሩ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል። ሰለሞን ሙጬ መግለጫውን ተከታትሎታል።


ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ