1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ሕወሓት» እና «ኦነግ ሸኔ» በአሸባሪነት እንዲፈረጁ የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 25 2013

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የውሳኔ ሀሳቡን የሚያፀናውና ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ ፍ/ቤቶች ብዙ ሰዎች ያለአግባብ እንዳይንገላቱ በሕግ እና ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ጥንቃቄ የተሞላበት ተጠያቂነት እንዲያስከትል ተጠይቋል።የውሳኔ ሀሳቡን ከማፅደቁ በፊትም ጉዳዩን በጥልቀት መርምሮና ማስረጃዎችን ጠይቆ ኃላፊነት የተሞላው ውሳኔ ሊያሳልፍ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

https://p.dw.com/p/3suBy
Karte Äthiopien englisch

«ሕወሓት» እና «ኦነግ ሸኔ» በአሸባሪነት እንዲፈረጁ የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በሕግ ባለሞያዎች እይታ

በሚኒስትሮች ምክር ቤት በአሸባሪነት እንዲፈረጁ የውሳኔ ሀሳብ የቀረበባቸው ሕወሓት እና 'ሸኔ' ውሳኔው ከፀና በረጅም ጊዜ ሂደት የሕዝብ ፀጥታ ፣ የአገር ሠላም ሥጋት መሆናቸው ይቀንሳል ተባለ።ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሳኔ ሀሳቡን የሚያፀናውና ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ ፍርድ ቤቶች ብዙ ሰዎች ያለአግባብ እንዳይንገላቱ በሕግ እና ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ጥንቃቄ የተሞላበት ተጠያቂነት እንዲያስከትሉ ጠይቀዋል።ምክር ቤቱ የውሳኔ ሀሳቡን ከማፅደቁ በፊት ጉዳዩን በጥልቀት መርምሮና ማስረጃዎችን ጠይቆ ኃላፊነት የተሞላው ውሳኔ ሊያሳልፉ እንደሚገባ ጠቁመዋል።እንደ የሕግ ባለሙያዎቹ ገለፃ ፣ይህ ካልተደረገ ቀደም ሲል የተሻረው የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ላይ የተስተዋለው፣ሕጉን ለፖለቲካ ጥቅም ማዋልን ሊያስከትል ይችላል።የሚኒስትሮች ምክር ቤት ቅዳሜ ዕለት ባወጣው መግለጫ «ሕወሓት እና ሸኔ የተባሉት ድርጅትና ቡድን ሕዝብን ስጋትና ፍርሃት ውስጥ በመጣል በመንግሥት ላይም እምነት በማሳጣት የሀገረ መንግሥቱን ኅልውና አደጋ ላይ ጥለዋል» ሲል ከሷቸዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ