1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሕወሓት አልዋሃድም እንዳለ ቀረ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 27 2012

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በአስቸኳይ ጉባኤው የኢሕአዴግ ውህደት እንደማይቀበለው የመጨረሻ የተባለ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ 'የህወሓት አስቸኳይ ጉባኤ' 1066 አባላቱ ተሳትፈውበታል፡፡ 

https://p.dw.com/p/3VmvM
Äthiopien nach TPLF Meeting
ምስል DW/M. Haileselassie

«ከብልጽግና ጋር በጋራ መስራት አንችልም» ሕወሓት

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በአስቸኳይ ጉባኤው የኢሕአዴግ ውህደት እንደማይቀበለው የመጨረሻ የተባለ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ የሕወሓት ጉባዔ ትላንት ማምሻውን አስቸኳይ ስብሰባውን ሲያጠናቀቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ ኢሕአዴግ 'በክህደት' ፈርሷል፤  ብልፅግና ከተባለው ፓርቲ ጋር በጋራ ለመስራት አንችልም ብሏል፡፡ ሕወሓት ብልፅግና ፓርቲን «አዲስ፣ ሕገ-ወጥና ጥገኛ» ፓርቲ ሲል ገልፆታል፡፡በቀጣይም ከኢህአዴግ ጋር በተዛመደ የነበረው ሃብትና ንብረት ክፍፍል በሕጋዊ መንገድ እንደሚያስኬድ አስታውቋል፡፡
 ሕወሓት የሚመራው የክልል መንግሥት ከፌደራል መንግሥት ጋር ያለው ግንኙነት ሕግ በሚፈቅደው አካሄድ ብቻ ይመራል ያለው ፓርቲው ከዚህ ውጭ የሚፈጠር የተለየ ነገር ተቀባይነት አይኖረውም ሲል ጠንከር ያለ አቋም መያዙን አስታውቋል፡፡ የህወሓት ከፍተኛ የስልጣን ባለቤት የሆነው 'የህወሓት አስቸኳይ ጉባኤ' 1066 አባላቱ ተሳትፈውበታል፡፡ 


ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

 
ታምራት ዲንሣ
አዜብ ታደሰ