1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሕ/ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር እና የአፍሪቃ ቀንድ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 16 2010

በሕገ ወጥ መንገድ እየተካሄደ ያለው የጦር መሳሪያ ንግድ እና ዝውውር ለአፍሪቃ ቀንድ ሀገራት ሰላም እና ምጣኔ ሀብት እድገት መሰናክል ነው ተባለ። በዚሁ አካባቢ ሕገ ወጡ የጦር መሳሪያ ንግድ በተለይ በጅቡቲ መስፋፋቱም ነው የተገለጸው።

https://p.dw.com/p/33b0B
Afrika  EXX Africa	 Logo
ምስል Exx Africa

«የመሳሪያው ፍላጎት በዋነኝነት የሚመጣው ከሶማልያ እና ከተለያያዩ ያካባቢ ዓማፅያን ቡድኖች ነው።»

ይህን ያስታወቀው  ከአፍሪቃ ጋር የንግድ ልውውጥ ለማድረግ ለሚፈልጉ ምዕራባውያን መንግሥታት እና የግል ዘርፍ ተቋማት በአህጉሩ ስላለው የደህንነት እና የንግድ ስራ ሁኔታ ምክር የሚሰጠው ኤክስ ኤክስ አፍሪካ የተባለው ድርጅት ነው። ይህን በተመለከተ ድርጅቱ ባወጣው ልዩ ዘገባ መሰረት፣ ብዙው የጦር መሳሪያ ወደ ጅቡቲ የሚገባው የርስበርስ ጦርነት ከሚካሄድባት የመን ነው።

ድልነሳው ጌታነህ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ