1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኅብረተ ሰብየመካከለኛው ምሥራቅ

ሒውማን ራይትስዎች በሳዑዲ ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች 

ዓርብ፣ ሐምሌ 23 2013

በሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ተባብሶ የቀጠለው እንግልትና ስቃይ አሳስቦኛል ሲል ሂውማን ራይትስ ዋች ገለፀ። በድርጅቱ የፍልሰተኞች መብት ተመራማሪ ናድያ ሃርድማን እንዳስታወቁት በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በደል በተመለከተ ድርጅታቸው ለሳዑዲ መንግስት ሪፖርት ቢያቀርብም ምላሽ አላገኘም

https://p.dw.com/p/3yKne
Human Rights Watch Logo Symbolbild
ምስል Getty Images/AFP/J. Macdougall

ሒውማን ራይትስዎች በሳዑዲ ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች 

በሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ተባብሶ የቀጠለው እንግልትና ስቃይ አሳስቦኛል ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች ገለፀ።
በድርጅቱ የስደተኞችና ፍልሰተኞች መብት ተመራማሪ ናድያ ሃርድማን በተለይ ለዶይቸ ቬለ እንዳስታወቁት በኢትዮጵያውያን ስደተኞቹ ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በደል በተመለከተ ድርጅታቸው ለሳዑዲ መንግስት ሪፖርት ቢያቀርብም እስካሁን ምላሽ አላገኘም። በኢትዮጵያኑ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የመብት ረገጣ ተከታትሎ የማጋለጡን ተግባር ድርጅታቸው አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተመራማሪዋ ጠቁመዋል። 

ታሪኩ ኃይሉ
ሸዋዬ ለገሰ