1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሐረር ከተማ ቃጠሎ የተጎዱ ነጋዴዎች ሰዎች ስሞታ 

ሐሙስ፣ ነሐሴ 2 2011

በሐረሪ ብሔራዊ ከልላዊ መስተዳድር ሀረር ከተማ በሚገኘው መብራት ኃይል የገበያ ማዕከል ከወራት በፊት የደረሰበት ቃጠሎ በርካቶችን ሀብት ንብረታቸውን አውድሞ አውላላ ሜዳ ላይ ጥሏል ፡፡ የገበያ ማዕከሉ አሁን በሚገኝበት መብራት ኃይል በተባለው ቦታ እንኳ ቃጠሎ ሲገጥመው ሁለተኛ ጊዜው ነው ፡፡

https://p.dw.com/p/3NavU
Äthiopien Wiederaufbau des Harrar-Marktes
ምስል DW/Mesay Teklu

የቃጠሎዉ መጠን ይለያይ እንጂ ችግሩ ባንኳኳበት ቤት ክፉ አሻራን ጥሎአል


በሐረሪ ብሔራዊ ከልላዊ መስተዳድር ሐረር ከተማ በሚገኘው መብራት ኃይል የገበያ ማዕከል ከወራት በፊት የደረሰበት ቃጠሎ በርካቶችን ሀብት ንብረታቸውን አውድሞ አውላላ ሜዳ ላይ ጥሏል ፡፡ የገበያ ማዕከሉ አሁን በሚገኝበት መብራት ኃይል በተባለው ቦታ እንኳ ቃጠሎ ሲገጥመው ሁለተኛ ጊዜው ነው፡፡ መልካም እንደልሆነ አጋጣሚ ደግሞ በሁለቱም የአደጋ  ክስተት ንብረታቸው ተቃጥሎ የተጎዱ ወገኖች አሉ ፡፡ በማዕከሉ ላይ የደረሰውን ቃጠሎ እና ጉዳት ተከትሎ መልሶ የማቋቋም ስራ እንደሚሰራ የተናገረው የክልሉ መንግስት ከቀደመው ግዜ በተሻለ ፍጥነት የወደሙ ቤቶችን መልሶ በቆርቆሮ የመገንባት ስራ መጀመሩ ጥሩ ተስፋ አጭሯል ፡፡ መጠኑ ይለያይ እንጂ ችግሩ ባንኳኳበት ቤት ክፉ አሻራን ጥሎ ባለፈው በዚህ ቃጠሎ የተጎዱ ሰዎች አሁን መገንባት በጀመረው በዚህ የገበያ ሱቅ ደስተኛ ቢሆኑም መንግስት ሊደርግ የሚገባው ነገር ስለመኖሩ ይጠቅሳሉ ፡፡
በሌላ በኩል ነጋዴዎቹ መደበኛ ስራቸውን ለመጀመር የብድር ገንዘብ እየተመቻቸ ስለመሆኑ መስማታቸውን ገልፀዋል ፡፡ ምንም እንኳን እስካሁን ተግባራዊ ባይደረግም ፤ ብድር ከችግሩ አገግሞ ወደ ስራ ለመግባት አያስችልም የሚሉት ነጋዴዎች መንግሥት የተለየ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልሀኪም አብዱማሊክ ለ«DW» በስልክ እንደገለፁት የክልሉ መንግሥት ችግሩን በአጭር ግዜ ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ ሰርቷል ፡፡ ብድር ጫና ይፈጥራል የሚል ቅሬታ ስለመነሳቱ ያነሳሁላቸው ኃላፊው አብዛኞቹ ቀደም ሲል ከተቋሙ የወሰዱትን ብድር የመለሱ መሆናቸውን አረጋግጠናል ብለዋል ፡፡ የአሁኑ ብድርም ለመስጠት ዝግጁ መደረጉን ጠቁመዋል ፡፡ የገበያ ማዕከሉ መልሶ ግንባታ እየተካሄደ በሚገኝበት ቦታ ተገኝቼ እንደተመለከትኩት እንዳንዶቹ ሱቆች በር በመግጠም ሥራ ለመጀመር ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ተመልክቻለሁ ፡፡

Äthiopien Wiederaufbau des Harrar-Marktes
ምስል DW/Mesay Teklu

መሳይ ተክሉ 
አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሠ