1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሎውሮ ባግቦ፣ የአይሲሲ ውሳኔ እና የዓ/ሕግ ተቃውሞ

ረቡዕ፣ ጥር 8 2011

የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት፣ አይሲሲ  ዓቃብያነ ሕግ ፍርድ ቤቱ በስብዕና አንጻር በተፈጸሙ ወንጀሎች የተመሰረቱባቸውን  ክሶች ትናንት የሰረዘላቸው የቀድሞው  የኮት ዲቯር ፕሬዝደንት ሎውሮ ባግቦ ወደ ሀገራቸው እንዳይመለሱ እንዲያግድ ጠየቁ። ዓቃብያነ ሕጉ በትናንቱ ውሳኔ አንጻር ይግባኝ የማለት እቅድ እንዳላቸው ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3Bfoa
Gebäude des Internationalen Strafgerichtshofs Den Haag
ምስል picture-alliance/dpa

ሎውሮ ባግቦ፣ የአይሲሲ ውሳኔ እና የዓ/ሕግ ተቃውሞ


የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት፣ አይሲሲ ዳኞች ካለፉት ሰባት ዓመታት ወዲህ በዘ ሄግ በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው  የኮት ዲቯር ፕሬዝደንት ሎውሮ ባግቦ በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። ዳኞቹ ውሳኔአቸውን እና የውሳኔአቸውን ምክንያቶች በይፋ ካወጡ በኋላ ይግባኝ እንደሚሉ ነው ያስታወቁት።  ባግቦ አንዴ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ወደ ዘ ሄግ ላይመለሱ ይችላሉ የሚል  ስጋት እንዳላቸው የአይሲሲ ቃል አቀባይ ፋዲ ኤል አብደላ ተናግረዋል። 
«ዓቃቤ ሕግ በውሳኔው፣ ክሶቹ በተሰረዙበት  አንጻር ይግባኝ የሚልበት አጋጣሚ አለ። ይህ ብቻ አይደለም ችሎቱን በእስር ቤት እንዲቆዩ የተለየ ሁኔታ መኖሩን የሚደግፍ መደገፍ ከቻለ  በ ልዩ በሆነ መንገድ ሊጠይቅም ይችላል። »
እንደሚታወሰው፣ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት፣ አይሲሲ በቀድሞው  የኮት ዲቯር ፕሬዝደንት ሎሮ ባግቦ እና በወጣቶች ጉዳይ ተመልካች ሚንስቴር ሻርል ብሌ ጉዴ ላይ በጎርጎሪዮሳዊው 2010 ዓም  ከተካሄደው ምርጫ በኋላ በስብዕና አንጻር በተፈጸሙ ወንጀሎች የተመሰረቱባቸውን አራት ክሶች  በጠቅላላ ሰርዟል። ችሎቱን የመሩት ዳኛ ኩኖ ታርፉሰር የተከሳሾች ጠበቆች ማስረጃዎቻቸውን ገና ሳያቀርቡ በፊት ነበር ተከሳሾቹ የ73 ዓመቱ ባግቦ እና የ47 ዓመቱ ጉዴን ነፃ በማለት  ወዲያውኑ እንዲፈቱ ያዘዙት።
የድህረ ምርጫው ቀውስ ሰለባዎችም እንደ ዓቃብያነ ሕጉን ባግቦ /ፈቱ የተባለበትን  የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንደተቃወሙት ካሪም የተባለው ሰላ,ባ ገልጸዋል።። 
 «ባግቦ ነፃ መለቀቅ የለባቸውም።ምክንያቱም ከተለቀቁ ፍትህ ለማግነት የምናደርገው ጥረታችን መና ይቀራል። ስለዚህ ባግቦ እንዲቀጡ እና ፍትህ እውን እንዲሆን እንፈልጋለን። »
ሰለባዎቹ የተሰባሰቡበት ቡድን ፕሬዚደንት ኢሲያካ ዲያቢም ቡድናቸው  ፍትህ ለማግኘት የጀመረውን ጥረት እንደሚቀጥሉ በማስታወቅ ልክ እንደ ዓቃቤ ሕጎቹ ውሳኔውን አጣጥለውታል።
«ሎውሮ ባግቦ እና ሻርል ብሌ ጉዴ ይፈቱ የተባለበትን ውሳኔ እንቃወማለን። ምክንያቱም በርካታ ሁኔታዎች እንደሚጠቁሙት እነዚህ ሰዎች አንዴ ከተለቀቁ ይጠፋሉ። »
ውሳኔው የድህረ ምርጫ ውዝግብ ሰለቦችን እጅግ ቅር ያሰኘ መሆኑን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምዕራብ እና ማዕከላይ አፍሪቃ ዳይሬክተር ማሪ ኤቨሊን ፔትሩስ ባሪ ገልጸዋል።
በአንጻሩ ፣ውሳኔውን እንደ  ትልቅ ድል መመመልከታቸውን የባግቦ ጠበቃ ኤማኑዌል አልቲት ተናግረዋል።
«« አዎ፣ በውሳኔው በጣም ተደስተናል። ምክንያቱም በዓለም ሁሉም እውነቱን አውቆታል፣  ለደንበኛችን እና ለእውነቱ እና ለኮት ዲቯር  ሰላም  ጭምር የሚበጅ ፍትሕ እውን ሆኗል። እዚህ ውሳኔ ላይ መደረሱ በጣም ትልቅ ነገር ነው ምክንያቱም ለዚያች ሀገር እርቀ ሰላም እና ሰላም ለማስገነት ይረዳል።»
የፍርዱን ሂደት በዴን ኸግ ፍርድ ቤት ደጃፍ እና በአቢዦ በቴሌቪዥን ሲከታተሉ የነበሩት የባግቦ እና የሻርል ብሌ ጉዴ ደጋፊዎች በነሱ ላይ ተመስርቶ የነበረው ክስ በጠቅላላ በቋረጡ ደስታቸውን ሲገልጹ ውለዋል። 
«ካለባግቦ እርቀ ሰላም ሊኖር አይችልም። እሳቸው ብቻ ናቸው እርቀ ሰላም ሊያወርዱ የሚችሉት።»
ባግቦ በአይሲሲ ፊት የቀረቡ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት  ሲሆኑ፣ በከፍተኛ ስልጣን ላይ ያሉ መሪዎችን ሳይቀር ፍርድ ፊት ማቅረብ እንደሚቻል ያሳየ ትልቅ ጥረት ነበር የተቆጠረው። 
ኮት ዲቯር በ2010 ዓም  ምርጫ ካካሄደች እና ባግቦም በአላሳን ዋታራ የደረሰባ,ውን ሽንፈታቸውን መቀበል አሻፈረኝ ካሉ በኋላ አበተከተሉት አራት ወራት በዘለቀው ዉዝግብ  ከ3000 የሚበልጡ ሰዎች ተገድለዋል። 

Elfenbeinküste, Simone Gbagbo
ምስል Getty Images/S.Kambou
Kombibild - Charles Blé Goudé und Laurent Gbagbo

አርያም ተክሌ

ተስፋለም ወልደየስ