1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ልዩ ቃለ-ምልልስ ከኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር

ረቡዕ፣ ጥቅምት 12 2012

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከዶይቼ ቬለ (DW) ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የደህንነት ባለስልጣኖቻቸው በቂ መረጃ ይሰጧቸው እንዳልነበር ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3RnrN
Hailemariam Desalegn, ehemaliger äthiopischer Ministerpräsident
ምስል DW

ልዩ ቃለ-ምልልስ ከኃይለማርያም ደሳለኝ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በዶይቼ ቬለ (DW) ቴሌቪዥን ጣቢያ ከሚተላለፈው “ኮንፍሊክት ዞን” ከተባለ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “አምባገነን ተብዬ ልጠራ አይገባኝም” ብለዋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በእርሳቸው የስልጣን ዘመን ስለተፈጸሙ ግድያዎች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና የሙስና ወንጀሎች ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል። እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ የደህንነት ባለስልጣኖቻቸው በወቅቱ በቂ መረጃ ይሰጧቸው እንዳልነበር ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ አሁን ያለው ለውጥ እንዲመጣ የራሴን ድርሻ ተወጥቻለሁ” ያሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር “እኔን አምባገነን አድርጎ መሳል ትክክል አይደለም” ብለዋል። አቶ ኃይለማርያም በዚምባቡዌ ሃራሬ ከቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም ጋር መገናኘታቸውን በተመለከተም ጥያቄ ተነስቶላቸው ነበር። የ“ኮንፍሊክት ዞኑ” ቲም ሴባስቲያን ከኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ካደረገው ሰፋ ያለ ውይይት ውስጥ የተወሰነውን ቀንጭበናል። 

ቃለ ምልልሱን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።    

ተስፋለም ወልደየስ 

እሸቴ በቀለ