1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ልዕልት የኔንጋ

Richard Tiéné
ሐሙስ፣ ነሐሴ 14 2012

በአሁኑ ጊዜ ቡርኪና ፋሶ የሞሲ ህዝብ እናት የሆኑትን ልዕልት የኔንጋን የሚያወሱበት በርካታ ማስታወሻዎች አሏቸዉ።አፍሪቃ ሴት ተዋጊዎች ያሏት የነበረ ቢሆንም የኔንጋ ግን እንዲሁ በቀላሉ ከዚህ መደብ የሚጠቃለሉ ብቻ አይደሉም።

https://p.dw.com/p/3hFUC
African Roots | Yennenga

ልዕልት የኔንጋ መቼ ተወለዱ?
የታሪክ ምሁራን ልዕልት የኔንጋ የተወለደበትን ጊዜ እርግጠኛ አይደሉም። ግን በርካቶች በ 11 ኛው እና በ 15 ኛው ክፍለ ዘመን መካከል ነበር በሚለው ይስማማሉ። የልዕልቷ አባት ንጉስ ናባ ኔዴጋ ከልጆቻቸው ሁሉ አስበልጠው የሚወዷቸው እሳቸውን ነበር። ንጉሱ በአሁኒቷ ጋና የምትገኘው የዳጎምባ ሥርወ መንግሥትን ያስተዳድሩ ነበር። 

ስለ ልዕልት የኔንጋ ለየት የሚለው ነገር ምንድን ነው?

African Roots | Yennenga

በአፈ ታሪክ መሠረት ፈረስ ልዕልቷ ከልጅነታቸው አንስቶ የሚወዱት እንስሳ ነበር። ከብዙ ሙከራዎች በኋላም አባታቸውን መጋለብ እንዲማሩ ለማሳመን ችለዋል። ይህ በሥርወ መንግሥቱ ለወንዶች ብቻ የተሰጠ መብት ነበር።  ከዚያም ልዕልቷ አስደናቂ የፈረስ ጋላቢ ብቻ ሳይሆኑ እጅግ አስደናቂ ተዋጊም መሆናቸውን አሳዩ። የወለዱት ወንድ ልጅ ደግሞ ከአንድ አዳኝ ጋር ጫካ ውስጥ የነበራቸው የፍቅር ውጤት ነው።  የፍቅራቸውን ታሪክ ያሰመረው ፈረስ ስለነበርም ልጃቸውን «ኦድራጎ» ብለው ጠሩት ትርጓሜው ወንድ ፈረስ ማለት ነው። አድራጎ ቡርኪና ፋሶ ውስጥ ትልቁ የጎሳ ቡድን የሆነው የሞሲ ሰዎች የዘር ሀገር ምንጭ ነው።
ስለ እሳቸው ታሪክ አወዛጋቢ ነገር ምንድን ነው?
የኔንጋ ጫካ ውስጥ ስለጠፉበት አጋጣሚ አሁንም የተለያዩ ትረካዎች አሉ። በጣም ዝነኛ የሆነው ግን በጣም የሚወዷቸው አባታቸው ሊድሯቸው ፍቃደኛ ስላልነበሩ - ከአባታቸው ለማምለጥ ሲሉ መንደራቸውን ትተው እንደሸሹ ነው። 
የፍቅረኛቸውን አመጣጥ በተመለከተ አንዳንድ ምንጮች ከማሊ የመጡ ዶዞ (አዳኝ) ነበሩ ሲሉ ይገልጿቸዋል። ይህም ምናልባትም ለምን የሞሱ ህዝቦች የማሊ የዘር ሀገር እንዳላቸው አመላካች ይሆናል። 
ምን አይነት ቅርስ ትተው አለፉ?
ለልዕልቷ ከፍተኛ ክብር ካሳዩ የቡርኪና ፋሶ አርቲስቶች መካከል ይሊ ናሞ አንዷ ናት። ለእሷ የኔንጋ ማለት « ደፋር እና ፍርሃት የሌላት ሴት፣ አማዞናዊ፣ ልንመስላት የምንፈልጋት ሴት ማለት ነው።» ድምፃዊቷ ለመጀመሪያዋ አልበም ስም ስታወጣም የልዕልቷን ስም መርጣለች። ይህም “የዛሬዎቹ የኔንጋ ነን የምንልበት መንገድ” ይሰኛል። 
የኔንጋ ቅርስ “የኔንጋ ወርቃማው ፈረስ” በሚል ሽልማት በአፍሪቃ ሲኒማ ክብረ በዓል (FESPACO) አማካኝነት አሁንም በሕይወት እንዲቆይ ተደርጓል። አዲስ የኔንጋ የተባለች ከተማም በመቋቋም ላይ ትገኛለች። ASFA የኔንጋ ፣ የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግ የመጀመሪያው ምድብ ስም፣የብሔራዊ እግር ኳስ ቡድኑ  "The Stallions" ለኝህ ልዕልት እና ተወዳጁ እንስሳ ማስታወሻ መድረክ ይሰጣሉ።

ልዕልት የኔንጋ፦ የሞሲ ሥርወ መንግሥት መሥራች

ልዕልት የኔንጋ

ይህ ዘገባ አፍሪካዊ ሥረ-መሠረት በሚል ከጌርዳ ሔንክል ተቋም ጋር በመተባበር የሚቀርብ ዝግጅት ነው። የዘገባው ሳይንሳዊ ምክር የተገኘው ከፕሮፌሰር ጉዳዬ ኮናቴ፣ ሊሊ ማፌላ Ph.D እና ፕሩፌሰር ክሪስቶፈር ኦግቦግቦ ነው።