1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ላምሮት ከማል በዋስ እንድትለቀቅ ተወሰነ 

ሐሙስ፣ ኅዳር 9 2014

የአቃቤ ሕግና የተከሳሽ ጠበቆች ክርክር በስር ፍርድ ቤት ቀጥሎ ዛሬ አዲስ አበባ ያስቻለዉ ፍርድ ቤት ተከሳሽዋ በ5ሺሕ ብር ዋስ ተለቅቃ እንድትከራከር በይኗል።

https://p.dw.com/p/439TY
Äthiopien Oberlandesgericht Lideta
ምስል Seyoum Getu/DW

የፍርድ ቤቱ ሙግት ዓመት ከመንፈቅ ሊሞላዉ ነዉ

ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴደሳን በመግደል ወይም በማስገደል በአራተኛ ተጠርጣሪነት ተከስሳ የነበረችዉ ላምሮት ከማል በዋስ እንድትፈታ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ። አቃቤ ሕግ በላምሮት ላይ ለመሰረተዉ የአሸባሪነት ክስ በቂ መረጃ አላገኘንም ያሉት የፌደራሉ ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ከዚሕ ቀደም ክሱን ዉድቅ አድርገዉት ነበር። የአቃቤ ሕግና የተከሳሽ ጠበቆች ክርክር በስር ፍርድ ቤት ቀጥሎ ዛሬ አዲስ አበባ ያስቻለዉ ፍርድ ቤት ተከሳሽዋ በ5ሺሕ ብር ዋስ ተለቅቃ እንድትከራከር በይኗል።

ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ