ሊቢያ የሰፈሩ ስደተኞች መገደል
ሐሙስ፣ ሰኔ 27 2011ማስታወቂያ
ሊቢያ ርዕሠ ከተማ ትሪፖሊ አጠገብ በሚገኘዉ ታጁራ መጠለያ ጣቢያ የተጠለሉ ስደተኞች ትናንት በጦር ጄት ተደብብድበዉ መገደላቸዉን የተለያዩ የስደተኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች ማዉገዛቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ።ትናንት በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ተሰይሞ የነበረዉ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታዉ ምክር ቤትም ሆነ፣ መንግሥታት ግን እስካሁን ግድያዉን አላወገዙም።ግብፅ፣ሳዑዲ አረቢያ፤የተባበሩት አረብ አሚራት እና ፈረንሳይ ይደግፏቸዋል የሚባሉት የጦር አበጋዝ ኻሊፋ ሐፍጣር የጦር ጄቶች እንደጣሉትን በሚታመነዉ ቦምብ 44 ስደተኞች ተገድለዋል።ከ130 በላይ ቆስለዋል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ