1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ ድጋፍ በበርሊን

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 21 2010

ዛሬ ጀርመን መዲና በርሊን ውስጥ የጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ የለውጥ ሒደትን በመደገፍ በቀድሞው የጀርመን አውሮፕላን ጣቢያ በአሁኑ ጊዜ የሕዝብ መናፈሻ በኾነ አካባቢ ኢትዮጵያውያን ተሰብስበው አምሽተዋል።

https://p.dw.com/p/32FYo
Deutschland -Treffen von  Äthiopischen Diaspora-Mitglieder in Berlin
ምስል DW/Y. H-Hinz

ድጋፍ ለጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ

ዛሬ ጀርመን መዲና በርሊን ውስጥ የጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ የለውጥ ሒደትን በመደገፍ በቀድሞው የጀርመን አውሮፕላን ጣቢያ በአሁኑ ጊዜ የሕዝብ መናፈሻ በኾነ አካባቢ ኢትዮጵያውያን ተሰብስበው አምሽተዋል። ኢትዮጵያውያን በውጭ ሃገራት ከተሞች በተለምዶ ብዙውን ጊዜ መንግሥትን ሲቃወሙ ነበር መስማት የተለመደው። ዛሬ ግን የኢትዮጵያውያኑ መሰባሰብ ለተቃውሞ አይደለም። ኢትዮጵያውያኑን በበርሊን ያሰባሰባቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የተጀመረው የለውጥ ሒደት እንደሆነ ተሳታፊዎቹ ገልጠዋል። አዲሱ አመራር በኢትዮጵያ የጥላቻ እና የመጠፋፋት ግንቡን ደርምሶታል፤ ለዛም ነው ለድጋፍ የተሰባሰብነው ብለዋል ከተሳታፊዎቹ አንዱ። በሥፍራው የተገኘው የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ-ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬው ነበር።

ሙሉ ቃለ መጠይቁ ከታች የድምጽ ማዕቀፉ ውስጥ ይገኛል።

ይልማ ኃይለ-ሚካኤል

ማንተጋፍቶት ስለሺ