1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ለዉጥ

ማክሰኞ፣ መስከረም 29 2011

ህወሓትንም መሩ።ከቅርብ ጓዶቻቸዉ ጋር ባለመጣጣማቸዉ የመሠረቱ እና የመሩትን ፓርቲ፤ ኢትዮጵያንም ጥለዉ ተሰደዱ።እንደገና ትምሕርት።ዛሬ የፖለቲካ ሳይንስ ዶክተር ናቸዉ

https://p.dw.com/p/36BGL
Addis Abeba
ምስል Haile

«ለዉጡን የሚደግፉት ... ጥቂት ናቸዉ» ዶ/ አረጋዊ በርሔ

ፖለቲካን የተቀየጡት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፖለቲካ  ሲያጠኑ ነዉ።ኋላ ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) የተባለዉን የቀድሞ አማፂ ቡድን፣ በ1960ዎቹ ማብቂያ ከመሠረቱ ጥቂት ወጣቶች አንዱ ናቸዉ። ትምሕርት ወይም ጥናቱን ትተዉ ፖለቲካዉን በነፍጥ ትግል ቀጠሉበት።ህወሓትንም መሩ።ከቅርብ ጓዶቻቸዉ ጋር ባለመጣጣማቸዉ የመሠረቱ እና የመሩትን ፓርቲ፤ ኢትዮጵያንም ጥለዉ ተሰደዱ።እንደገና ትምሕርት።ዛሬ የፖለቲካ ሳይንስ ዶክተር ናቸዉ።በ2001 ያሳተሙት መፅሐፍ ህወሓት የሐገር መሪነቱን ሥልጣን እስከጨበጠበት ጊዜ ድረስ የነበረ ፖለቲካዊ ታሪኩን የሚዘክር ነዉ።ዶክተር አረጋዊ በርሔ።ዛሬም ፖለቲከኛ ናቸዉ።የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር የተሰኘዉ ፓርቲ መሪ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ሸንጎ አባል ናቸዉ።አዲስ አበባን ምናልባትም ዘመድ ወዳጆቻቸዉንም ከ43 ዓመታት፤ የትግራይን ጫካ ከ30 ዓመታት በኋላ በቅርቡ ዳግም አዩት።ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ ትዝብት፤ትዝታ፤ ምክር እቅዳችዉን ነገረዉናል። አዳምጡት።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ