1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለእጓለ ምውታን የሚደረግ ርዳታ

ዓርብ፣ ጥቅምት 16 2011

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ወላጅ አልባ ህጻናትን ለመርዳት ከቀድሞ በበለጠ ጥረቷን አጠናክራ እንደምትሰራ አንድ የቤተክርስትያኒቱ ባለስልጣን አስታወቁ። በሀገሪቱ በተለያዩ ምክንያቶች ወላጅ አልባ የሆኑት 4,6 ሚልዮን ህጻናት ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/37GD2
Sitz des Patriarchen der äthiopisch-orthodoxen Kirche in Addis Abeba
ምስል DW

ለእጓለ ምውታን የሚደረግ ርዳታ

ቤተክርስትያኒቷ እነዚህን ወላጅ አልባ ህጻናት ለመርዳት የወጠነችውን እቅድን ለማሳካትም በርዳታ ላይ ብቻ ጥገኛ ሳትሆን፣ ህብረተሰቡን በማስተባበር ራሷን ችላ መቆም እንዳለባት ባለስልጣኑ ጠቅሰዋል። ከቤተክርስትያኒቱ ርዳት ተጠቃሚ የሆኑ DW ያነጋገራቸው ሁለት ተረጂዎች ያገኙትን ድጋፍ አሞግሰው፣ እነሱም ወደፊት ሌሎች ችግረኞችን ለመርዳት ከቤተክርስትያኒቷ ጋር እንደደሚተባበሩ ገልጸዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ