ለኢትዮጵያ ችግር ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ የተቋቋመ የሰላም ቡድን
ቅዳሜ፣ ጥር 7 2014ማስታወቂያ
ከእስር የተፈቱትን ጨምሮ በፖለቲካ ልዩነቶች በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙ አካላት እና መንግስት ተቀራርበው በመወያየት ለአገር ዘላቂ ሰላም እንዲሰሩ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች እና የሰላም እናቶች የተሰኘ የምክክር መድረክ ጠየቀ፡፡
ከአገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የኃይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች ዛሬ በአዲስ አበባ በዝግ ስመክር ውለው በመጨረሻም የደረሱበት የመግባቢያ ነጥቦች ላይ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
መንግስት በቅርቡ ፖለቲከኞችን ከእስር ለመፍታት የጀመረውን የአገሪቱ የሰላም ጥረቶችን እንደሚደግፉና መንግስት ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም የሰላም ቡድኑ ጠይቀቋል፡፡
በኢትዮጵያ አመትን የተሻገረው ጦርነት በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል የፈጠረውን መቃቃር ለመፍታት በቅርቡ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው አገራዊ ምክክር ጉልህ ድርሻ እንዲጫወትም ጥሪ ቀርቧል፡፡
ስዩም ጌቱ
ታምራት