1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለኢትዮጵያ ችግር ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ የተቋቋመ የሰላም ቡድን

ቅዳሜ፣ ጥር 7 2014

ከእስር የተፈቱትን ጨምሮ በፖለቲካ ልዩነቶች በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙ አካላት እና መንግስት ተቀራርበው በመወያየት ለአገር ዘላቂ ሰላም እንዲሰሩ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች እና የሰላም እናቶች የተሰኘ የምክክር መድረክ ጠየቀ፡፡

https://p.dw.com/p/45aUr
Äthiopien | Aufruf zur Versöhnung
ምስል Seyoum Getu/DW

መንግስት እና የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ንግግር እንዲመጡ የሚጠርቅ ውይይት ተከናወነ

ከእስር የተፈቱትን ጨምሮ በፖለቲካ ልዩነቶች በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙ አካላት እና መንግስት ተቀራርበው በመወያየት ለአገር ዘላቂ ሰላም እንዲሰሩ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች እና የሰላም እናቶች የተሰኘ የምክክር መድረክ ጠየቀ፡፡

ከአገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የኃይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች ዛሬ በአዲስ አበባ በዝግ ስመክር ውለው በመጨረሻም የደረሱበት የመግባቢያ ነጥቦች ላይ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

Äthiopien | Aufruf zur Versöhnung
መንግስት በቅርቡ ፖለቲከኞችን ከእስር ለመፍታት የጀመረውን የአገሪቱ የሰላም ጥረቶችን እንደሚደግፉና መንግስት ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም የሰላም ቡድኑ ጠይቀቋል፡፡ምስል Seyoum Getu/DW

መንግስት በቅርቡ ፖለቲከኞችን ከእስር ለመፍታት የጀመረውን የአገሪቱ የሰላም ጥረቶችን እንደሚደግፉና መንግስት ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም የሰላም ቡድኑ ጠይቀቋል፡፡

በኢትዮጵያ አመትን የተሻገረው ጦርነት በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል የፈጠረውን መቃቃር ለመፍታት በቅርቡ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው አገራዊ ምክክር ጉልህ ድርሻ እንዲጫወትም ጥሪ ቀርቧል፡፡

ስዩም ጌቱ 

ታምራት