1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለአውሮፓ ኤኮኖሚ ማገገሚያ 500 ቢሊዮን ዩሮ እንዲዘጋጅ ጀርመን እና ፈረንሳይ ሐሳብ አቀረቡ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 11 2012

የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኤማኑዌል ማክሮ የአውሮፓ ምጣኔ ሐብት በኮሮና ሳቢያ ከገጠመው ቀውስ እንዲያገግም 500 ቢሊዮን ዩሮ እንዲዘጋጅ ሐሳብ አቅርበዋል።

https://p.dw.com/p/3cU5A
EU Merkel und Macron | Aufbauprogramm für Europa
ምስል REUTERS

አውሮፓ እና ጀርመን

የጀርመን መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኤማኑዌል ማክሮ የአውሮፓ ኮሚሽን 500 ቢሊዮን ዩሮ ተበደሮ ለአውሮፓ እንዲያቀርብ ግፊት እያደረጉ ነው። ሁለቱ መሪዎች ምክረ ሐሳቡን ይፋ ያደረጉት በትናንትናው ዕለት ነው።

የኮሮና ወረርሽኝ ላስከተለው ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ቀውስ የመፍትሔ ሐሳብ ለማቅረብ ዘገምተኛ ነበር እየተባለ ለሚወቀሰው የአውሮፓ ኅብረት ሁለቱ መሪዎች ያቀረቡት ሐሳብ መልካም ዕድል ነው ተብሏል። በሜርክል እና ማክሮ ሐሳብ መሠረት የአውሮፓ ኮሚሽን ገንዘቡን ከካፒታል ገበያ ተበድሮ ለአባል አገራት ያቀርባል።

ገበያው ንጉሴ

እሸቴ በቀለ