1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለአማራና አፋር ተፈናቃዮች የቀይ መስቀል ድጋፍ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 18 2013

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በአፋር እና አማራ ክልሎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃይ ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገለፀ። እንዲያም ሆኖ ግን የቀይ መስቀል ድጋፍ አነስተኛ መጠን ያለው መሆኑን ተፈናቃዮች ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/3zQdO
Symbolbild Hilfsorganisationen in Afghanistan
ምስል picture alliance/Tone Koene

የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ርዳታ

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በአፋር እና አማራ ክልሎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃይ ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገለፀ። በጦርነቱ የሚፈጸመውን ግድያ፤ ንብረት ማውደም እና ዘረፋውን ሸሽተው በችግር ላይ ለሚገኙ ዜጎች የመሰረታዊ የመጠለያ፣ የማብሰያ እንዲሁም የአልባሳት ድጋፍ እያደረገ ምሆኑም ተጠቅሷል። አብዛኛዎቹ ተፈናቃዮች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውንም ኮሚቴው ተናግሯል። በከባድ ጦር መሣሪያ በታገዘው ጦርነት በርካቶች መሞታቸውን የየክልሉ መንግሥታት ገልጠዋል። በጦርነቱ ለሚቆስሉ፣ ለሚታመሙ እና እንክብካቤ ለሚያሻቸው ዜጎች የጤና ተቋማት የተፈጠረባቸውን መጨናነቅ ለማቃለል ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የቁሳቁስ አቅርቦት እየተሰጠ መሆኑን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። እንዲያም ሆኖ ግን የቀይ መስቀል ድጋፍ አነስተኛ መጠን ያለው መሆኑን ተፈናቃዮች ይናገራሉ። 
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ