1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለቦይንግ 737 ሰለባ ቤተሰቦች ካሣ ጥያቄ

ዓርብ፣ ነሐሴ 3 2011

በኢትዮጵያ ከወራት በፊት በተከሰከሰው የቦይንግ 737 MAX 8 አውሮፕላን ሕይወታቸውን ላጡ  ሁለት ቤተሰቦች ጥብቅና የቆሙ አካላት የካሣ  ክፍያ ጥያቄ  አቀረቡ። የሕግ ባለሙያዎቹ የካሣ ጥያቄውን ያቀረቡት ለዩናይትድ ስቱትስ የፌደራል አቪየሽን  አስተዳደር  ነው።

https://p.dw.com/p/3NfB1
Äthiopian Airlines Boeing  737 Max 8
ምስል picture-alliance/AP Photo/M. Ayene

«ጥያቄው ለዩናይትድ ስቱትስ የፌደራል አቪየሽን ቀርቧል»

በአሜሪካን ሕግ አንድን የመንግሥት አካል ከመክሰስ በፊት ያጠፋኸውን ጥፋት ጠቅሶ ሊከፈል የሚገባው የገንዘብ  ካሣ መጠን ተጠቅሶ በማመልከቻ መጠየቅ እንደሚቻል ያመለከቱት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪው አቶ ሸክስፒር ፈይሳ፤ በዚሁ መሠረት የካሣ ጥያቄውን ማቅረባቸውን ለዶይቼ ቬለ DW ገልጸዋል።  ከአምስት ወራት በፊት እንደተነሳ ብዙም ሳይቆይ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በተከሰከሰው ቦይን አውሮፕላን  የበረራ ሠራተኞችን ጨምሮ 157 ሰዎች ተሳፍረው ነበር። በጉዳዩ ላይ የሕግ ባለሙያውያን ያነጋገረው የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን  ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

 ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ