1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለሶርያ እና ሩስያ ከየኔቶ የቀረበ ጥሪ

ዓርብ፣ የካቲት 20 2012

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (በምህጻሩ ኔቶ) ፣ሶሪያ እና ሩስያ በሰሜን ምሥራቅ ሶሪያ የሚያደርጉትን የአየር ድብደባ እንዲያቆሙ ጠየቀ። ኔቶ ጥሪውን ያስተላለፈው 33 የቱርክ ወታደሮች ሶሪያ ውስጥ ትናንት በአየር ድብደባ ከተገደሉ በኋላ ድርጅቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ነው።

https://p.dw.com/p/3Yc4V
Syrien Sarakeb Rauch nach Angriffen in der Provinz Idlib
ምስል Reuters/U. Bektas

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (በምህጻሩ ኔቶ) ፣ሶሪያ እና ሩስያ በሰሜን ምሥራቅ ሶሪያ የሚያደርጉትን የአየር ድብደባ እንዲያቆሙ ጠየቀ። ኔቶ ጥሪውን ያስተላለፈው 33 የቱርክ ወታደሮች ሶሪያ ውስጥ ትናንት በአየር ድብደባ ከተገደሉ በኋላ ድርጅቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ነው። የኔቶ ዋና ፀሀፊ የንስ ስቶልትንበርግ በሶሪያዋ ኢድሊብ ክፍለ ሃገር የሶሪያ መንግሥት እና የሩስያ የጦር ጄቶች የቱርክ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ የሚያደርጉትን ድብደባ አባል ሃገራት እንደሚያወግዙ አስታውቀው ጥቃቱ እንዲቆምም ጥሪ አቅርበዋል።
« ጥቃቱን እንዲያቆሙ ፣የዓለም አቀፍ ሕግን እንዲያከብሩ እና የተመድ ለሰላማዊ መፍትሄ የሚያደርገውን ጥረት እንዲደግፉ እጠይቃለሁ። ይህ አደገኛ ሁኔታ መርገብ አለበት ።እናም በአስቸኳይ ወደ 2018 ቱ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲመለሱ እንማጸናለን።»
በትናንቱ የአየር ጥቃት የተገደሉት የቱርክ ወታደሮች ቁጥር ከእስካሁኑ ከፍተኛው ነው።28ቱ የድርጅቱ አባላት በሶሪያ የአየር ድብደባ በተገደሉት የቱርክ ወታደሮች የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል። ኔቶ በሶሪያ የአየር ቅኝት ከማድረስ በስተቀር በሶሪያው ጦርነት ቀጥተኛ ሚና የለውም።አባል ሃገራት ግን ቱርክ በሶሪያ በምታደርገው በእጅጉ ተከፋፍለዋል፤አውሮጳውያን አጋሮችም ቱርክ ስደተኞችን ትለቅብናለች የሚል ስጋት ላይ ናቸው።ግሪክ የድንበር ቁጥጥሯን ማጥበቋ ተሰምቷል። የቱርክ ፕሬዝዳንት ጠይብ ሬሴፕ ኤርዶጋን ቃል አቀባይ ከሶሪያው ጥቃት በኋላ ቱርክ ስደተኞችን ከአሁን በኋላ መያዝ አትችልም ብለዋል። ቱርክ ከአውሮጳ ህብረት ጋር ባደረገችው በ2016 ባደረገችው ስምምነት 3.6 ሚሊዮን የሶሪያ ስደተኞችን አስጠግታለች። 

Belgien Brüssel NATO Generalsekretär Jens Stoltenberg
ምስል picture-alliance/AP Photo/O. Matthys

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ