1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 3 2011

ዲ ደብሊው ያነጋገራቸው የኤኮኖሚ ምሁር እንዳሉት ችግሩ ሀገሪቱን ለበጀት ጉድለት ከማጋለጡም በተጨማሪ መፍትሄ ካልተፈለገለትም በምጣኔ ሀብት እድገቷ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀርም። ቁጥጥሩ በተጠናከረበት በአሁኑ ጊዜ፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሕገ ወጥ መንገዶች ገንዘብ የማሸሽ እና የማዛወር ሙከራ ተባብሶ መቀጠሉ ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/39yDP
Äthiopien Leiter des Ministeriums für Finanzkommunikation Addis Yirga
ምስል DW/S. Muchie

ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና አደጋው

ኢትዮጵያ በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት ለተለያዩ ምጣኔ ሀብታዊ ችግሮች እንደምትጋለጥ አንድ ምሁር አስታወቁ። ዲ ደብሊው ያነጋገራቸው የኤኮኖሚ ምሁር እንዳሉት ችግሩ ሀገሪቱን ለበጀት ጉድለት ከማጋለጡም በተጨማሪ መፍትሄ ካልተፈለገለትም በምጣኔ ሀብት እድገቷ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀርም። የኢትዮጵያ የገቢዎች ሚኒስቴር ለዲደብሊው በሰጠው መግለጫ ቁጥጥሩ በተጠናከረበት በአሁኑ ጊዜ፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሕገ ወጥ መንገዶች ገንዘብ የማሸሽ እና የማዛወር ሙከራ ተባብሶ መቀጠሉን አስታውቋል። ለዚህም ሰሞኑን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከኢትዮጵያ ገንዘብ ለማስወጣት እና ለማስገባት የተደረጉ ሙከራዎችን መስሪያ ቤቱ በአብነት አቅርቧል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ በዚህ ላይ ያተኮረ ዘገባ አዘጋጅቷል። 
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ