1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሁለተኛ የምርጫ ቀን ይፋ ሆነ

ዓርብ፣ ሰኔ 4 2013

ቦርዱ አገሪቱ በገጠማት የፀጥታ መናጋት ችግር በሌላ በኩል "ቦርዱን ሀዘን ውስጥ የከተተ" ባለው የመራጮች ህትመት ወረቀት ላይ በተፈጠረ የህትመት የአፈፃፀም ችግር ነው ብሏል። ጉዳዩ"በጣም የሚያሳዝን" መሆኑን የገለፀው ቦርዱ በሶማሌና ሐረሪ ክልሎች ድምፅ አሰጣጡ ሰኔ 14 ቀን ቀርቶ ጳጉሜን 1 ቀን 2013 ዓ.ም በሁለተኛው ዙር ይከናወናል ብሏል።

https://p.dw.com/p/3ukeI
Äthiopien Sidama stimmen für Teil-Autonomie
ምስል AFP/M. Tewelde

ሁለተኛው ዙር የድምፅ መስጫ ዕለት ጳጉሜን 1 ቀን 2013 ዓ.ም ሆኖ ነዉ

ስድስተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ በአገሪቱ የምርጫ ታሪክ በሁለት የየለያዩ ዕለታት የሚደረግ ምርጫ ሆኖ እንዲከናወን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ወሰነ። ቦርዱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው አንድም አገሪቱ በገጠማት የፀጥታ መናጋት ችግር በሌላ በኩል ደግሞ "ቦርዱን ሀዘን ውስጥ የከተተ" ባለው የመራጮች ህትመት ወረቀት ላይ በተፈጠረ የህትመት የአፈፃፀም ችግር ነው ብሏል። ጉዳዩ "በጣም የሚያሳዝን" መሆኑን የገለፀው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሶማሌ እና ሐረሪ ክልሎች ሙሉ በሙሉ ድምፅ አሰጣጡ ሰኔ 14 ቀን መሆኑ ቀርቶ ጳጉሜን 1 ቀን 2013 ዓ.ም ሆኖ በተወሰነው በሁለተኛው ዙር የድምፅ መስጫ ዕለት ይከናወናል ብሏል። የድምፅ አሰጣጡ በሁለት ዙር መደረጉ በምርጫ ሕጉ ላይ የተቀመጠ አሰራር መሆኑን ግን ቦርዱ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል። በአምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ የሚፈፀመው የደቡብ ምዕራብ ሕዝበ ውሳኔም ጳጉሜን 1 ቀን 2013 ዓ.ም በሁለተኛው ዙር የድምፅ መስጫ ዕለት ይከናወናል። 

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ