1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የDW አካዳሚ ፕሮጀክት በትግራይ

ሰኞ፣ ሰኔ 10 2016

ዶቼቬሌ አካዳሚ ወይም ዲዳብሊው አካዳሚ በምስራቅ አፍሪካ ለሚገኙ የተሻለ የለውጥ ሀሳብ ይዘው ለሚቀርቡ አካላት ባደረገው ጥሪ የተሳተፈችው ብርሃን፥ ያቀረበችው የፆታ ጥቃት ሰለባ የሆኑ በትግራይ የሚገኙ ሴቶች ተጠቃሚ የማድረግ ሐሳብ ተቀባይነት አግኝቶ ወደ ተግባር ስራ መግባቷ ትገልፃለች።

https://p.dw.com/p/4h9tG
Mekelle |  "She Heals, We Heal", Deutsche Welle Akademie
ምስል Million Hailessilasie/DW

የDW አካዳሚ ፕሮጀክት በትግራይ

በትግራይ በጦርነቱ ወቅት የፆታ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች፥ በድጋፍ ማጣት በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ መሆናቸው ይገለፃል። እነዚህ የፆታ ጥቃት ሰለሰዎች ለማገዝ የሚረዳ የተባለ ከዲዳብሊው አካዳሚ ጋር በመተባበር የሚሰራ ፕሮጀክት ይፋ ተደርጓል።

በትግራይ በጦርነቱ ወቅት በተለይም በሴቶች ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ አስገድዶ መድፈር እና የተለያዩ ፆታ ተኮር ጥቃቶች መፈፀማቸው ዓለምአቀፍ ተቋማት፣ የመብት ተሟጓቾች እና ሌሎች ሲገልፁ ቆይተዋል። በትግራይ ክልል በኩል የሚወጡ ጥናቶች በጦርነቱ ወቅት ከ120 ሺህ በላይ የትግራይ ሴቶች ላይ ፆታ መሰረት ያደረገ ጥቃት መፈፀሙ ያመለክታሉ። ከጦርነቱ መቆም በኃላም ቢሆን እነዚህ ሰለባዎች በአስከፊ ሁኔታ ላይ መሆናቸው የሚገለፅ ሲሆን ይህ የተረዱ የተወሰኑ አካላት ትኩረታቸው እዚህ ላይ አድርገው ይሰራሉ። ብርሃን ገብረክርስቶስ ላለፉት ከሶስት በላይ ዓመታት በበጎ ፍቃደኝነት በጦርነቱ ወቅት የፆታ ጥቃት የደረሳቸው ሴቶች በማገዝ፣ በደላቸው በመሰነድ፣ ከጥቃቱ ስቃይ እንዲወጡ በመርዳት ተግባራት ላይ የተሰማራች ናት። ዶቼቬሌ አካዳሚ ወይም ዲዳብሊው አካዳሚ በምስራቅ አፍሪካ ለሚገኙ የተሻለ የለውጥ ሀሳብ ይዘው ለሚቀርቡ አካላት ባደረገው ጥሪ የተሳተፈችው ብርሃን፥ ያቀረበችው የፆታ ጥቃት ሰለባ የሆኑ በትግራይ የሚገኙ ሴቶች ተጠቃሚ የማድረግ ሐሳብ ተቀባይነት አግኝቶ ወደ ተግባር ስራ መግባቷ ትገልፃለች።

የDW አካዳሚ ፕሮጀክት በመቐለ ሲጀመር
የDW አካዳሚ ፕሮጀክት በመቐለ ሲጀመርምስል Million Hailessilasie/DW

የፆታ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶች ላይ የምትሰራው ብርሃን ገብረክርስቶስ፥ ሰለባዎቹ ከደረሰባቸው ጥቃት በዘለለ እንዴት መዳን እንዳለባቸው እውቀቱ እንደሌላቸው፣ ከመረጃ የራቁ መሆናቸው የምታነሳ ሲሆን ይህ ለማገዝ በሬድዮ ተደራሽ የሚሆን እና ሰለባዎቹ መረጃ የሚያገኙበት፣ የመዳን ምክር የሚሰጥበት ስርጭት በቀጣዮ ሳምንት እንደሚጀመር ትገልፃለች።

ፈትሊ የሬድዮ ፕሮግራም የተሰኘው ይህ ስርጭት፥ በመቐለ በሚገኝ ሞሞና ኤፍኤም ጣብያ መሰራጨት የሚጀምር ሲሆን፥ ይህንኑ ለማድረግ ደግሞ ከተቋሙ ጋር ስምምነት ተደርሷል። የፆታ ጥቃት ጉዳይ አሁንም አሳሳቢ መሆኑ የምትገልፀው ብርሃን፥ መልኩ ቀይሮ ከጦርነቱ በኃላ ጭምር በትግራይ በስፋት እየታየ ያለ ነው ትላለች። ተጠያቂነት ማስፈን ደግሞ ከሚመለከታቸው እንደሚጠበቅ በጎ ፍቃደኛዋ ትገልፃለች።
ሚልዮን ሃይለስላሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ