«CPJ» የድሪደዋ ጋዜጠኞች ጥቃት እንዲመረመር ተጠየቀ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 17 2010ማስታወቂያ
በድሬዳዋ መገናኛ ብዙኃን የጋዜጠኞች ቡድን ላይ የተፈፈፀዉን ጥቃት መንግስት እንዲያጣራ ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተዉ ድርጅት «CPJ» ጠየቀ። በጥቃቱ የጋዜጠኞች ቡድኑን ያሰፈረዉን መኪና ሲያሽከረክር የነበረዉ ሱሊማን መሃመድ በደረሰበት ጉዳት ሲሞት ሌሎች አምስት መኪና ዉስጥ የነበሩ ሰዎች መቁሰላቸዉ ተያይዞ ተዘግቦአል። በቡድኑ ላይ ጥቃት የተፈጸመዉ የኤርትራዉ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ለመዘገብ ቡድኑ ሐምሌ ስድስት ቀን ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ነበር ። «CPJ» እንደዘገበዉ ጋዘጠኞቹን ያሳፈረችዉ መኪና በኦሮሚያ ክልል ሚኤይሶ ከተማ ስትደረስ ማንነታቸዉ ያልታወቁ ሰዎች መኪናዋን አስቁመዉ ተሳፋሪዎቹን ደብድበዋል።
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ