CPJ-አሳሳቢዉ የጋዜጠኞች መብት ጥሰት
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 7 2005ማስታወቂያ
ተቋሙ ሰሞኑን ሁለት ጋዜጠኞች ለእስራት መዳረጋቸዉ በፕሪስ ነፃነት ላይ የተደረገ ጥቃት ነዉ ሲል ገልጾአል። የዋሽንግተን ዲሲዉ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዘገባ ልኮልናል። ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከላካይ ኮሚቴ CPJ፤ ሁለት ጋዜጠኞች ከሁለት ሳምንታት በላይ ያለክስ መታሰራቸዉ እንዳሳሰበዉ ነዉ የገለፀዉ። የተቋሙ የአፍሪቃ ጉዳዮች አስተባባሪ መሃመድ ኬዬታ፤ የነዚሁ ጋዜጠኞች እስራትን በተመለከተ እንደተናገሩት « በሐምሌ 26 ቀን የኢትዮጵያ የደህንነት ኃይሎች ለራድዮ ቢላል የሚሰሩትን ሁለት ጋዜጠኞች፤ ደርሴማ ሶልንና፤ ካሊድ ሞሃመድን አስረዋቸዋል። የሙስሊም ፀረ- መንግስት ተቃዎሞ የዜና ሽፋን ሲሰጡ ነበር። እናም በደህንነት ሃይሎች ተይዘዉ አዲስ አበባ በፖሊስ ጣብያ ዉስጥ በእስር ላይ ይገኛሉ»
አበበ ፈለቀ
አዜብ ታደሰ
ሒሩት መለሰ