CDU ፓርቲና የቀረበበት የገንዘብ ጥያቄ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 25 2003ማስታወቂያ
በአገር ዉስጥ ገቢ ከቀረጥና ግብር ከህዝብ ተሰብስበዉ በመንግስት በኩል ወጪ የሚደረግ ማንኛዉም ገንዘብ የት እንደደረሰ ብሎም ህዝቡ የመጠየቅ መብቱ በህግ የሠፈረ ነዉ። የዛሬ አራት ዓመት በራይንላንድ ፋልስ ክፍለ ሃገር የክርስቲያን ዴሞክራት ፓርቲ በጀርመንኛ ምህፃሩ CDU ገንዘብ አላግባብ ለምርጫ ድግስ አዉጥቷል ተብሎ ተከሷል። ፓርቲዉ አላግባብ አወጣ የተባለዉ ገንዘብ አራት መቶ ሺ ዩሮ መሆኑ ሲገለጽ ከነቅጣቱ ከሚሊዮን ዩሮ በላይ መክፈል ይጠበቅበታል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ