9 የተቃውሞ ፓርቲዎች ስምምነት
ረቡዕ፣ ጥቅምት 12 2007ማስታወቂያ
ተባብረው ለመሥራት የተፈራረሙት ፓርቲዎች፤ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፤(መኢአድ) የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት(መአሕድ)፤ መአዴፓ ሰማያዊ ፓርቲ፤ የሶዶ ጎርደና ሕዝብ ዴሞካራሲያዊ ድርጅት፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ፤ የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሕብረት የከምባታ ሕዝብ ኮንግረስ ናቸው።
የትብብሩ አመራር አባላት፤ ከዚህ ቀደም የነበሩ ጥምረቶችን ድክመቶች በመፈተሽ፤ በጋራ ለመሥራት ሲስማሙ፤ ከዚህ ቀደም የተቃውሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣ መተቸትን የማይቀበሉ ነበሩ። በነጻው ፕረስ ሳይቀር ተቃዋሚዎችን መተቸት ኢ ህ አ ዴ ግ ን ያጠናክራል የሚል አስተሳሰብ ነበረና ይህን አስተሳሰብ ሰብረን ወጥተናል ማለታቸውን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የላከልን ዘገባ ያስረዳል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ