1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

5780ኛ የአይሁዳዉያን አዲስ ዓመት ተከበረ

ሐሙስ፣ መስከረም 22 2012

«ሮሽ ሀሻና» ማለት ምን ማለት ነዉ ፤ በጥሬ ትርጉሙ? አዲስ ዓመት ወይም የወራቶች ራስ ማለት ነዉ። እስራኤላዉያን ባለፈዉ እሁድ ምሽት ላይ ጀምሮ 5780ኛዉን አዲስ ዓመት ተቀብለዋል በድምቀት አክብረዋል።

https://p.dw.com/p/3QhCP
Rosch ha-Schana  der jüdische Neujahrstag
ምስል DW/M. Assefa

ሮሽ ሀሻና ማለት በይብራይስጥ አዲስ ዓመት ማለት ነዉ

«እስራኤል የሚገኙ ቤተ ኢትዮጵያዉያን ቤተ -እስራኤሎች ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ ቤተ- እስራኤሎች ግንኙነት በመፍጠር እንዲረዱ በማድረግ ፀሎት ቤቶች እንዲከፈቱ በማድረግ፤ ከዛም ባለፈ ወደ እስራኤል የሚገቡበትን ሁኔታ ለማመመቻቸት ትልቅ ስራ እየተሰራ ነዉ»

Rosch ha-Schana  der jüdische Neujahrstag
ምስል DW/M. Assefa

አልያህ ቤት» የተሰኘ ስለ ቤተ-እስራኤላዉያን መጽሐፍ የጻፉ እና በቤተ እስራኤላዉያን ጉዳይ ላይ የተለያዩ ጥናቶችን በማድረግ ላይ የሚገኙት አቶ መስፍን አሰፋ ነበሩ።

እስራኤላዉያን ባለፈዉ እሁድ ምሽት ላይ ጀምሮ 5780ኛዉን አዲስ ዓመት ተቀብለዋል በድምቀት አክብረዋልም።  የእስራኤላዉያኑ አዲስ ዓመት  «ሮሽ ሀሻና» ይባላል።  የእስራኤላዉያኑ አዲስ ዓመት አከባበር ምን ይመስላል ፤ በእስራኤልም ሆነ በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ-እስራኤላዉያንስ ሮሽ ሀሸናን አልያም የእስራኤልን አዲስ ዓመት እንዴት ያከብሩታል።  ስለቤተ-እስራኤላዉያን የተለያዩ ጥናቶችን በማድረግ ላይ ያሉ ባለሞያን አነጋግረናል።

Rosch ha-Schana  der jüdische Neujahrstag
ምስል DW/M. Assefa

በእስራኤላዉያን ጉዳይ የተለያዩ ጥናቶችን በማድረግ ላይ የሚገኙትና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ስብሰባዎችን የሚካፈሉት ቤተ-እስራኤላዊዉ አቶ መስፍን አሰፋን ያገኘናቸዉ «ሮሽ ሀሻና» ማለት የእስራኤላዉያንን አዲስ ዓመት ለማክበር በዝግጅት ላይ ሳሉ ባለፈዉ ዓርብ እለት ነበር።

Rosch ha-Schana  der jüdische Neujahrstag
ምስል DW/M. Assefa

የአይሁዳዉያን አዲስ ዓመት ባለፈዉ ሳምንት እሁድ ምሽት ጀምሮ እንደየሁኔታዉ በተለይም በሌሎች ሃገራት ዉስጥ በሚገኙ አይሁዳዉያን ጋር እስከያዝነዉ ሳምንት ማክሰኞ እለት ድረስ እንደሚከበር የቤተ-እስራኤላዊ ታሪክ ተመራማሪው አቶ መስፍን አሰፋ ተናግረዋል።  በአይሁዳዉያን የቀን ቀመር ከባለፈዉ እሁድ ጀምሮ ፤5780ኛዉ ዓመት ላይ ደርሰናል።

Rosch ha-Schana  der jüdische Neujahrstag
ምስል DW/M. Assefa

«ሮሽ ሀሻና» ማለት ምን ማለት ነዉ ፤ በጥሬ ትርጉሙ? አዲስ ዓመት ወይም የወራቶች ራስ ማለት ነዉ ሲሉ አቶ መስፍን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ቤተ-እስራኤላዉያን ታሪክ ባህል ጉዳይ ከፍተኛ ጥናት በማካሄድ ላይ ያሉት አቶ መስፍን አሰፋ ለሰጡን ቃለ-ምልልስ በማመስገን ቤተ-እስራኤላዉያኑን ሁሉ ሮሸ ሀሸና በማለት ሙሉዉን መሰናዶ እንዲያደምጡ እንጋብለን!   

 

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ