49ኛዉ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ትርኢት በበርሊን
ዓርብ፣ ነሐሴ 29 2001ማስታወቂያ
ዛሪ በበርሊን 49ኛዉ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ትርኢት በመታየት ላይ ነዉ ። ይህ ለስድስት ቀናት የሚዘልቀዉ የተለያዩ ድንቅ ኤሌክትሮኒክስ ግኞች የሚታዩበት ኤግዚቢሽን ከ60 በላይ አገራትን በማሳተፍ ላይ ሲሆን 1164 ያህል የተለያዩ ድርጅቶች፣ የተለያዩ አዳዲስ ስራዎቻቸዉን ማቅረባቸዉ ተገልጾአል። ትናንት አመሻሽ ላይ በመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ተመርቆ የተከፈተዉን በአለማችን ድንቅ የተባለለትን ይህን የኤሌክትሮኒክስ ትርኢት ዛሪ የበርሊኑን ወኪላችን ይልማ ሃይለሚካኤል ጎብኞታል።