1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

33 ዓመታት በአሜሪካ የታሰረዉ ጀርመናዊ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 8 2012

የሁለት ሰዎች ሕይወትን አጥፍተሃል በሚል ከ 30 ዓመት በላይ በዩናይትድ ስቴትስ እስር ቤት የነበረዉ የ 53 ዓመቱ የንስ ሶሪግ ከእስር ተፈቶ ሃገሩ ጀርመን ገባ። የንስ ሶሪግ ዛሬም ስለወንጀሉ የሚያዉቀዉ ነገር እንደሌለ ነዉ የሚናገረዉ።  

https://p.dw.com/p/3Uyas
Deutschland | Ankunft Jens Söring am Flughafen Frankfurt
ምስል picture-alliance/AP Photo/M. Probst

የሁለት ሰዎች ሕይወትን አጥፍተሃል በሚል ከ 30 ዓመት በላይ በዩናይትድ ስቴትስ እስር ቤት የነበረዉ የ 53 ዓመቱ የንስ ሶሪግ ከእስር ተፈቶ ሃገሩ ጀርመን ገባ። የፍቅረኛዉን ወላጆች ገድለሃል በሚል ተጠርጥሮ ሲታሰር ለፍቅረኛዉ ሲል በመጀመርያ ወንጀሉን በማመኑ ነበር ለእስር የበቃዉ። ጀርመናዊዉ ከቀናት በኋላ ይህን የተናገረዉ ለቀድሞ ፍቅረኛዉ ሲል መሆኑን በመግለጽ ስለወንጀሉ የሚያዉቀዉ ነገር እንደሌለ ቢናገርም ምርመራዉ በእስር ለ 33 ዓመታት አቆይቶታል። የኋላ ኋላ የቨርጂኒያዉ ፍርድ ቤት የ 53 ዓመቱን ጀርመናዊ ሁለተኛ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በማስጠንቀቅያ ትናንት ከእስር ነፃ ለቆታል። ከሃገረ አሜሪካም ሁለተኛ እንዳይገመለስ ወደ ሃገሩ ጀርመን ተጠርዟል። ከ 8 ሰዓታት በረራ በኋላ ዛሬ እኩለ ቀን ጀርመን የገባዉ የንስ ሶሪግ አዉሮፕላን ማረፍያ ይጠባበቅ ለነበረዉ ደጋፊዎቹ እና ጋዜጠኞች «በሕይወቴ በጣም ከተደሰትኩባቸዉ እና እጅግ ጥሩ ከምላቸዉ ቀኖች መካከል የዛሬዋ ቀን ናት ነዉ ሲል ተናግሮአል። ሁለተኛም ወደ አሜሪካ መመለስ እንደማይፈልግ ገልፆአል። የንስ ሶሪግ ዛሬም ስለወንጀሉ የሚያዉቀዉ ነገር እንደሌለ ነዉ የሚናገረዉ።

Deutschland Ankunft Jens Söring am Flughafen Frankfurt
ምስል Reuters/T. Wagner

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ