32 ተጠርጣሪዎች ዋስ መከልከላቸዉ19 ሰኔ 2001ዓርብ፣ ሰኔ 19 2001የመንግስት ባለስልጣናትን ለመግደል አሲረዋል የሚለዉን ጨምሮ በርከት ያለ ክስ የተመሰረተባቸዉ፤ ከግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጋ በተገናኘ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች በፍርድ ቤት የዋስ መብት መከልከላቸዉን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ከአዲስ አበባ ዘግቧል።https://p.dw.com/p/Ibyoማስታወቂያአቃቤ ህግ 46 በሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ላይ አራት ክሶችን ያቀረበ ሲሆን በእስር ላይ የሚገኙትና ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት የእምነት ክህደት ቃላቸዉን ተጠይቀዋል። ታደሰ እንግዳዉ የፍርድ ቤቱን ዉሎ ተከታትሎ ዘገባ አድርሶናል። ታደሰ እንግዳዉ/ሸዋዬ ለገሠ ሂሩት መለሰ