1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

32ኛዋ የኔቶ አባል አገር በብራልስ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 3 2016

የስዊድንና የኔቶ ባለስልጣኖችና መሪዎች በተገኙበት በተካሄደ ስነስራት ባንዲራዋ ከሌሎች አባል አገሮች ባንዲራዎች ተርታ እንዲውለበለብ ተደርጓል። በስንስራቱ ላይ የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስተር ሚስተር ኡልፍ ክሪስቴርሶን ባሰሙት ንግግር፤ “ አሁን አባሎች እንጂ አጋሮች አይደለንም።

https://p.dw.com/p/4dRJm
ስዊድን የኔቶ አባል መሆንዋ በይፋ ከታወጀ በኋላ ብራስልስ ዉስጥ የነበረዉ ሥነ-ሥርዓት
ስዊድን፣ ለበርካታ ዘመናት ከኮሚንስቱም ከካፒታሊስቱን የጦር ተሻራኪ ድርጅቶች ሳትወግን ቆይታለች።አሁን ኔቶን ተቀየጠች ምስል Kenzo Tribouillard/AFP

32ኛዋ የኔቶ አባል አገር በብራልስ

 

ስዊድን ባለፈው ሳምንት የስሜን አትልናቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅትኔቶን 32ኛ አባል  በመሆን በይፋ ከተቀላቀለች በኋላ፤ ትንንት ብራሥልስ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ጽህፈት ቤት የስዊድንና የኔቶ ባለስልጣኖችና መሪዎች በተገኙበት በተካሄደ ስነስራት ባንዲራዋ  ከሌሎች አባል አገሮች ባንዲራዎች ተርታ እንዲውለበለብ ተደርጓል። በስንስራቱ ላይ የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስተር ሚስተር ኡልፍ ክሪስቴርሶን  ባሰሙት ንግግር፤ “ አሁን አባሎች እንጂ አጋሮች አይደለንም። ከሁለት መቶ አመት የገለልተኛ ፖሊሲ በኋላ፤ የዛሬው እለት ታሪካዊ እርምጃ የተወሰደበት  ነው። ይህ እንዲሆን ለብዙ አመታት ስንሰራበት ቆይተናል፤ በማለት፤ ኔቶን በመቀላቀሏ ስዊዲን ወደ ቤቷ ተመልሳለች፤ እኛ እናንተን እንደመረጥናችሁ ዛሬ እናንተም የመረጣችሁን መሆኑ የተረጋገጠበት ቀን ነው፤ በማለት ሁሉ ላንዱ አንዱ ለሁሉም የሚለውን የድርጁትን መርህ ጠቅስዋል።

የኔቶ ዋና ጸሃፊ ሚስተር ያን ስቶልቴንበርግ በበኩላቸው ባሰሙት ንግግር “ የስዊድንን ባንዲራ ከሌሎቹ አባል አገሮች ባንዲራዎች ተርታ ስናውለብለብ የሚሰማን የበለጠ አንድነትና ወንድማማችነት ነው በማለት  እሳቸውም ሁሉም ላንዱ አንዱ ለሁሉም በማለት ድርጅቱ ስዊዲንን በደስታ የተቀበላት መሆኑን አስትውቀዋል።

የስዊድን አባልነት ለኔቶ የሚያመጣው ተጨማሪ እሴት

ሚስተር ስቶልተንበርግ አክለውም የኔቶ አባልነት ለስዊድን፤  ለሰላሟና ደህንነቷ ዋስትና እንደሚሆን ሁሉ፤ ለድርጅቱም ትልቅ የጥንካሬ ምንጭ እንድሚሆን ዘርዝረዋል፤ “ ስዊድን ትልቅ የወታደር አቅም ነው ያላት፤  የባህር ሰርጓጅ መርከቦች ፤ ተዋጊ ጀቶች፤ የተሟላ ትጥቅ ያለው ሰራዊት ይዛ ነው የምትመጣው። ስለዚህ የድርጅቱ አባል በመሆኗ ኔቶ ተጠቃሚና የበለጠ ጠንካራ ነው የሚሆነው በማለት” ለሞስኮም የኔቶ በር ለሁሉም ክፍት መሆኑንና ወደ ድርጅቱ የሚገቡትን የሚወስኑት አባሎቹ እንጂ ሞስኮ ወይም ፕሬዝዳንት ፑቲን አለመሆናቸውን መልክት የሚያስተላልፍ መሆሆኑን አስታውቀዋል።

የስዊድን ብሔራዊ ባንዲራ ብራስልስ በሚገኘዉ የኔቶ ዋና መቀመጫ ትናንት በይፋ ተዉለብልቧል።
ከ200 ዓመታት በላይ የገለልተኝነት መርሕ ስትከተል የነበረችዉ ስዊድን የኔቶ አባል ሆነችምስል Kenzo Tribouillard/AFP

የስዊድን የገለልተኝነት ታሪክና የኔቶ አባል የሆነችበት ገፊ ምክኒያት

ስዊድን በአለም በገልተኝነትና በጸረ ጦርነት አቋሟ ስትጥቀስ የቆየች አገር ነች። ለሁለት መቶ አመታትና ከዚያም በላይ በሁለተኛው አለም ጦርነት ጊዜ ሳይቀር፤ ስዊድን የማንም የጦር ቡድን አባል ሳትሆን ነው የቆየችው። ከጥቂት አመታት ወዲህ በተለይም የሩሲያና ምዕራባውያን ውዝግብና ግጭት እያየለ ሲመጣና የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ሲጀመር ግን፤ የስዊድን መንግስትና ህዝብ  አስተያየት መለወጡና ወደ  ኔቶም ማንጋጠጥ መጀመሩ ነው የሚነገረው።  ካንድ አመት ተኩል በፊት የስዊድን መንግስት የኔቶ አባልነት ጥያቄ ሲያቀርብ ሁለት ሶስተኛው ስዊድናዊ  ጥያቄውን ይደግፈው እንድነበርም ታውቋል ።  ድጋፉም በዩክሬን ምክኒያት ምራባውያን ከሩሲያ ጋር የገቡበት ውዝግብና የተፈጠረው የጦርነት ድባብና ስጋት እንደሆነ ነው የሚገመተው።

አባልነቱንን የሚቃወሙ ወገኖች መከራከሪያ ሀሳብ

ይሁን እንጂ ስዊድን የምትታወቅበትን የገለልተኝነት ፖሊስዋን ትታ የጦር ድርጅት አባል መህኗ ያሳዛናቸውና የሚቃወሙም እንዳሉ ነው የሚታወቀው። እነዚህ ወገኖች አገራቸው የኔቶ አባል መሆኗ ይልቁንም ለጦርነትና ግጭት ሊዳርጋት ይችላል ባይ ናቸው። የፓራቦል መጽሄት ዋና አዘጋጅ  ካይሳ ኤኪስ ኤክማን  ወደ ኔቶ ለመግባት የተኬደበት መንገድ በራሱ  ያልተለመለደና ኢዶሞክራሲያዊ ነው “  ስለ የአውሮፓ ህብረት፤ ኢሮ፤ ህዝበ ውሳኔ ነበረን። በዚህ ትልቅ በሆነው የነኔቶ ጉዳይም ህዝበ ውሳኔ ማድረግ ነበረብን። በጥድፊያ ህዝቡ ሳይጠየቅና ሳይወስን ነው ከዚህ የተደረሰው፡  በማለት ውሳኔው የአብዛኛው ስዊድናዊ ፍላጎት ነው ሊባል እንደማይችል ነው የምትከራከረው።፡

ከአንድ መቶ አርባ መታት በላይ እድሜ እንዳለው የሚነገርለት የስውዲን የሰላም ማህብረሰብ ፟( Swidish peace and Arbitrtion Society) ፕሬዝዳንት ከርስቲን ቤርጊያ አስተያየት ደግሞ  ውሳኔው እንደውም ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ነው። “ በመሰረቱ ውሳኔው ታሪካዊ ስህተት ነው። ምክኒያቱም የኔቶ አባል መሆኑ ለስዊድንም ሆን ለአለም ሰላም ዋስትና አይሀንም። ይልቁም የበለጠ ውጥረት የሜፍጥርና ለጦርነት የሚያጋልጥ ነው የሚሆነው” በማለት የአገራቸው የሁለት መቶ አመት ገለልተኛ ፖሊሲ በዚህ  ሁኒታ ጥያቄ ውስጥ መግባቱ የሚያሳዝን መሆኑን ገልጸዋል።

ስዊድን የኔቶ አባል መሆንዋን የሚያበስረዉ ሥነሥርዓት በብራስልስ
ከቀኝ ወደ ግራ የኔቶ ዋና ፀሐፊ የንስ ሽቶልተንበርግና የስዊድን ጠቅላይ ሚንስትር ኡልፍ ክሪስተርሰን ብራስልስ-ቤልጂግምስል Kenzo Tribouillard/AFP

የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በአውሮፓ ውጥረት መፍጠሩና በገልተኛነታቸው የሚታውቁ አገሮችን ጭምር በስሜን አትላንቲክ ጦር ክቃል ኪዳን ድርጅት እንዲካተቱ ያደረገ ቢህንም በአካባቢው የተቀሰቀሰውን ጦርነት ባጭር ግዜ ማስቆም የሚችል መሆኑን ግን  ብዙዎች ይጠራጠርሉ። የኔቶ አባል አገሮች በተለይም አዲሶቹ የኖርዲክ አገራት ህዝቦችም ኔቶ የሚጠይቀውን ከፍተኛ ወጭና ወታደራዊ ግምባታ በመቃወምም ድምጻቸውን ማሰማት እንደሚጀምሩ ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት።

ገበያው ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር