1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

20 ሚሊዮን ኢትዮጵያ ርዳታ ይሻል-ኦቻ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 1 2014

በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች 9.4 ሚሊዮን ዜጎች እጅግ መሠረታዊ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸውም ድርጅቱ አመልክቷል። በመላው ኢትዮጵያም 20 ሚሊየን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/446Zw
Äthiopien Bericht über die humanitäre Arbeit
ምስል Solomon Muchie/DW

ስለሰብዓዊ ድጋፍ የተሰጠው ዝርዝር መግለጫ

በመላው ኢትዮጵያ 20 ሚሊየን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ተገለጸ። በተለይም በትግራይ፣ በአፋር እና አማራ ክልሎች 9,4 ሚሊየን ዜጎች እጅግ አስፈላጊ መሠረታዊ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸውም የብሔራዊ አደጋ ስጋር ሥራ አመራር ኮሚሽን እና በተመ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ በምህጻሩ ኦቻ ጉዳዩን አስመልክተው በጋራ በሰጡት መግለጫ ተመልክቷል። የተባበሩት መንግሥታት ኢትዮጵያ ውስጥ እንድ አላማ ብቻ እንዳለውና ያም የኢትዮጵያን ሕዝብ መደገፍ መሆኑን ተናገረ። የድርጅቱ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የሕይወት አድን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ከማቅረብ በተጨማሪ ለሰብዓዊ ቀውሶች ዘላቂ መፍትሔ የመፈለግ ተግባር ብቻ እንደሚያከናውን ገልጸዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች 9.4 ሚሊዮን ዜጎች እጅግ መሠረታዊ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸውም ድርጅቱ አመልክቷል። የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ርዳታ እንዲደርስ ከፍተኛ ሥራ እየሠራ ቢሆንም ሕወሓት ድጋፍ ጭነው የሄዱ ተሽከርካሪዎችን በማስቀረት ፣ መቀሌ እና ሽሬ ውስጥ ነዳጅን በጥቁር ገበያ እየሸጠ እንቅፋት መሆኑን የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሣ ተናግረዋል። ይህንን ድርጊት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በዝምታ ማለፉንም ተችተዋል።

 ሰሎሞን ሙጬ 

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ