17ኛዉ የዓለም ኤድስ ጉባኤ በሜክሲኮ
ሰኞ፣ ሐምሌ 28 2000ማስታወቂያ
የሰዎችን ህይወት እየተፈታተነ የሚገኘዉ የHIV ቫይረስ ከታወቀ ከ27ዓመታት ወዲህ የመረጃ ስርጭት፤ በሽታዉን የመከላከልና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የቫይረሱ ተጠቂዎች መድሃኒትም ሆነ ህክምና የማዳረሱ ጥረት ቀጥሏል። ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ ወገኖች እንደተናገሩት ግን ይህ ሁሉ ርብርብ በተለይም የድርጅቱን የምዕተ ዓመት የልማት ግብ ለማሳካትና የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ የአቅም እጥረት እየታየ ነዉ። በአንፃሩ ኢትዮጵያን መሰል በቫይረሱ ክፉኛ የተጎዱ አገራት ይዞታ ከዚህ አኳያ መሻሻል ያሳዩ ሲሆን እስከአዉሮጳዉያኑ 2010ዓ,ም ድረስም ሊደርሱበት ካለሙት ግብ ለመገኘት መፍጨርጨር ይዘዋል።