14ኛው የአፍሪቃ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር
ዓርብ፣ መጋቢት 6 2011ማስታወቂያ
ዛሬ በተጀመረው 14ኛው የአፍሪቃ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር ኢትዮጵያ 3 ወርቆችን በማግኘት ወድድሩን በድል ጀምራለች። የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ እማኛው ይግዛው ለ«DW» እንደገለጹት ዛሬ 4 ውድድሮች የተካሄዱ ሲሆን በ15 ኪሎ ሜትር ታዳጊ ሴቶች አንድ ኢትዮጵያዊትና አንድ ኤርትራዊት በተወዳደሩበት የብስክሌት ግልቢያ እትዮጵያ ወርቅ ስትወስድ ኤርትራ ደግሞ የብር ሜዳሊያ ወስዳለች። በ30 ኪሎ ሜትር ታዳጊ ዎንዶች ኢትዮጵያ ወርቅ፣ ኤርትራ ብር፣ሩዋንዳ ደግሞ የነሀስ አሸናፊ ሆነዋል። ከ23 ዓመት እደሜ በታች ሴቶች ኢትዮጵያ ወርቅ፣ ኤርትራ ብር፣ ደቡብ አፍሪካ ደግሞ የነሃስ ወስዳለች። ከ23 ዓመት እደሜ በታች ወንዶች ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ ወርቅ፣ሩዋንዳ ብር፣ ኢትዮጵያ የነሀስ ማሸነፏን አቶ እማኘው ተናግረዋል። ውድድሩ ነገም በሌሎች ርቀቶች እንደሚቀጥል ኃላፊው አመልክተዋል።
ዓለምነው መኮንን
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ