125ኛዉ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በባሕርዳር
ማክሰኞ፣ የካቲት 23 2013ማስታወቂያ
125ኛዉ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በአማራ መስተዳድር ባሕርዳር ዉስጥም በዓሉ በደማቅ ሥርዓት ተከብሯል።የባሕርዳሩ ወኪላችን ዓለምነዉ መኮንን እንደዘገበዉ እንደ አዲስ አበባዉ ሁሉ በባሕሩ በዓለም ላይ ወጣቶች፣ አባት አርበኞችና የአማራ ክልል ባለስልጣናት ተገኝተዋል።የአባት አርበኞችና የክልሉ ባለስልጣናት በየተራ ንግግር አድርገዋልም።ከተናጋሪዎቹ አንዱ የአማራ ክልል አባት አርበኞች ማሕበር ሊቀመንበር አቶ ዳኝነት አያሌዉ «የተማረዉ ክፍል ከዘር ፖለቲካና ሐገር ከመበጥበጥ» እንዲታቀብ አደራ ብለዋል።
ዓለምነዉ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ