125ኛዉ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በኦሮሚያ
ማክሰኞ፣ የካቲት 23 2013ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት በየአደባባዩ የፍቅር፣የመተሳሰብ፣ የመደጋገፍና የአንድነትን አስፈላጊነት የተናገሩበትን 125ኛዉ የአድዋ ድል በዓል ርዕሠ-ከተማ አዲስ አበባ ዉስጥ እንኳ በአንድነት አላከበሩትም።ከቀዳሚዉ ዘገባችን እንደተከታተላችሁት ብሔራዊዉ በዓል አዲስ አበባ አፄ ምኒሊክ መታሰቢያ አደባባይ ሲከበር፣ የኦሮሚያ መስተዳድር ደግሞ በዓሉን እዚያዉ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አክብሯል።የኦሮሚያ ርዕሠ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በበዓሉ ላይ ለታመደዉ በብዙ ሺሕ ለሚቆጠር ሕዝብ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ አስቸገሪ ጊዜ ላይ እንደምትገኝ ጠቅሰዉ፣ ይሁንና አሁንም ጀግና ትዉልድ ስላላት አትፈርስም ብለዋል።ታሪክም በሽለላና በፌስ ቡክ ጨዋታ አይሰራም-እንደ ርዕሠ መስተዳድሩ።
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ