1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

11ኛ የፌዴራል ክልል የማደራጀት ዝግጅት በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ ጥር 18 2013

በደቡብ ክልል አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ 11ኛ የፌደራሉ መንግስት አካል ሆነው ለመደራጀት እየተዘጋጁ መሆናቸውን ዐስታወቁ። የደቡብ ክልል መንግስት በበኩሉ የየዞኖቹ ሕዝብ የጋር ክልላዊ መንግስት ለማቆም ለሚያካሄዱት የቅደመና ድህረ-ሕዝበ ውሳኔ ሂደቶችን ያስተባብራል ያለውን ኮሚቴ በማደራጀት ወደ ሥራ መግባቱን ገልዷል።

https://p.dw.com/p/3oQgP
Karte Sodo Ethiopia ENG

አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ የሚያቋቊሙት ተብሏል

በደቡብ ክልል የሚገኙ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ 11ኛ የፌደራሉ መንግስት አካል ሆነው ለመደራጀት የሚያስችላቸውን መሰናዶ በማካሄድ ላይ አንደሚገኙ ዐስታወቁ። የደቡብ ክልል መንግስት በበኩሉ የየዞኖቹ ሕዝብ የጋር ክልላዊ መንግስት ለማቆም ለሚያካሄዱት የቅደመና ድህረ-ሕዝበ ውሳኔ ሂደቶችን ያስተባብራል ያለውን ኮሚቴ በማደራጀት ወደ ሥራ መግባቱን ገልዷል። የደቡብ ምዕራብ ክልል ሕዝበ ውሳኔ አስተባባሪ ኮሚቴ ምክትል ስብሳቢ አቶ ፀጋዬ ማሞ ለዶቼ ቬለ (DW) እንዳሉት ኮሚቴው ሕዝበ ውሳኔውን ከሚያስፈጽመው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመቀናጀት የማስተባበር ሥራውን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።ኮሚቴው በቀጣይ በሕዝበ ውሳኔው ውጤት መሰረት የሚዋቀረው ክልላዊ መንግስት ሊኖረው የሚገባውን ሕገ መንግስትና አስተዳደራዊ አወቃቀር ከወዲሁ የማዘጋጀት ሥራዎችን እንደሚያከናውን ምክትል ሰብሳቢው ተናግረዋል።  የሐዋሳው ዘጋቢያችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ዝርዝር ዘገባውን ልኮልናል።   

ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ