ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው ገቡ
ሰኞ፣ ግንቦት 13 2010ማስታወቂያ
ሳዑዲ አረብያ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቀረበላት ጥያቄ መሠረት ከእስር የፈታቻቸው ከአንድ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም፣ ባለፉት 3 ቀናት 1085 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ሀገራቸው መግባታቸውን ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያኑ የመጓጓዣ ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደየቤተሰቦቻቸው እንደተሸኙም ተገልጿል። ቃል አቀባዩን ያነጋገራቸው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ ልኳል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ